ወልዋሎ 3 ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንዲጫወት ቅጣት ተጣለበት

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አዲግራት ላይ መቀለ ከተማ ከ ፋሲል ከተማ ጋር ባደረጉት የከፍተኛ ሊግ 22ኛ ሳምንት ጨዋታ የተከሰተውን ረብሻ ተከትሎ ጥፋተኛ ነው ያለው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ላይ የገንዘብ እና በሜዳው ጨዋታ እንዳያደርግ ቅጣት ጥሎበታል፡፡

በጨዋታው በርካታ የወልዋሎ ደጋፊዎች የክለቡን ስም በመጥራት የፋሲል ከተማ ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች ላይ ጉዳት ለማድረስ በመሞከራቸው ፣ ዛቻ በመሰንዘራቸው እና ክለቡም በዚህ አመት የዲስፕሊን ግድፈት ሪኮርዶች ያሉበት በመሆኑ ቅጣት መጣሉን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

በውሳኔው መሰረት በሜዳው የሚያደርጋቸውን ቀጣይ 3 ጨዋታዎች በገለልተኛ ሜዳ እንዲያደርግ ፣ 30,000 ብር እንዲቀጣ እና ለደጋፊዎቹ የስፖርታዊ ጨዋነት ትምህርት በመስጠት ሪፖርት እንዲያደርግ ተወስኗል፡፡

የውሳኔው ዝርዝር ይህንን ይመስላል፡-

PicsArt_1467711084320

PicsArt_1467711114548

1 Comment

  1. ደደብ ፌዴሬሽን please soccer ethiopia መዘገብ ብቻ ሳይሆን ሚዛናዊነቱ ኣጣሩልን እስኪ ኣስቡ ደጋፊ እና ተጨዋቾች የደበደቡ ኣክሱም እና ዳሽን 25000 ምን ያልነካ ወልዋሎ 30000 እና 3ጨዋታ ኣስቡት ወልዋሎ የተጫወተው ከደብረብርሃንየወልዋሎ ስም በሌለበት ደጋፊዎቹ ስለጠሩ ቅጣት ኣፍረናል በዚህ ኣይነት ኣመራር መመራታችን

Leave a Reply