ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ መከላከያ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 0-3 መከላከያ
7′ አዲሱ ተስፋዬ 39′ ፍሬው ሰለሞን 78′ ሳሙኤል ታዬ


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በመከላከያ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ መከላከያ በፍፃሜው ቅዱስ ጊዮርጊስን ሀሙስ ይገጥማል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
89′
ሚካኤል ደስታ ወጥቶ ቴዎድሮስ ታፈሰ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
82′
መሃመድ ናስር ወጥቶ ማራኪ ወርቁ ገብቷል፡፡

80′ መሃመድ ናስር በመልሶ ማጥቃት በግሩም እንቅስቃሴ ወደ ሳጥን ገብቶ የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወጣበት፡፡

ጎልልል!!!
78′ ሳሙኤል ታዬ ግሩም ግብ አስቆጥሮ የመከላከያን መሪነት ወደ 3 አስፍቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
74′
ሳሙኤል ሳሊሶ ወጥቶ በሃይሉ ግርማ ገብቷል፡፡

70′ ዳኛቸው በቀለ ከቀኝ መስመር ከአምሃ ያሻገረለትን ኳስ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

69′ ንግድ ባንክ ኳሱን በሚገባ ተቆጣጥሮና ተጭኖ ቢጫወትም የመከላከያን ጠንካራ መከላከል ሰብሮ መግባት አልቻለም፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
62′
ቢንያም በላይ ወጥቶ አምሀ በለጠ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
59′
ፍቀረየሱስ ተወልደብርሃን ወጥቶ አብዱልከሪም መሃመድ ገብቷል፡፡

56′ ዳዊት አሰፋ የጎል ክልሉን ለቆ በመውጣቱ የፈጠረውን ስህተት ተጠቅሞ ፍሬው ከመሀል ሜዳ ቢሞክርም ለጥቂት ጎል ከመሆን ድናለች፡፡ ግሩም ሙከራ!
በነገራችን ላይ በሊጉ ሁለቱ ቡድኖች 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ሲለያዩ ሳሙኤል ታዬ የፌቮን ከግብ ክልሉ መውጣት ተመልክቶ ግብ ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
48′
ሰለሞን ገብረመድህን ወጥቶ ዳኛቸው በቀለ ገብቷል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በመከላከያ መሪነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

45′ አፍሬም ሆን ብለህ ወድቀሃል በማለት የዕለቱ ዳኛ የማስጠንቀቂያ ካርድ መዘዋል፡፡

ጎልልል!!!!!
39′ ፍሬው የመከላከያን መሪነት ወደ ሁለት አስፍቷል፡፡ ጦሩ የጥሎማለፍ ስፔሻሊስት መሆኑን በማሳየት ላይ ይገኛል፡፡

35′ ንግድ ባንኮች በተደጋጋሚ በረጅም ኳስ ወደ ሳጥን ውስጥ ለመግባት የሚያደርጉት ጥረት በመከላከያ ተከላካዮች እየከሸፈ ይገኛል፡፡

27′ ኢትዮዽያ ንግድ ባንክ የአቻነት ጎል ለማስቆጠር ከመከላክያ በተሻለ ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

20′ ጎል ከተቆጠረ በኋላ ጨዋታው በመሀል ሜዳ እንቅስቃሴ ተገድቦ ይገኛል፡፡

15′ አንዳንድ የአዳማ ተመልካቾች ስርአት ባለው መንገድ የሚሰማቸውን ሀሳብ በእለቱ ለተገኙት የፌዴሬሽኑ አመራሮች እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችንም በጭብጨባ እየሸኙ ይገኛሉ፡፡

ጎልልል!!!
7′ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ አዲሱ ተስፋዬ በግንባሩ በመግጨት ግሩም ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

5′ የመጀመርያዎቹ 5 ደቂቃ ቀዝቀዝ ብሎ የጀመረው ጨዋታ በፈጣን እንቅስቃሴ ተማሙቆ ቀጥሏል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በንግድ ባንክ አማካኝነት ተጀመረ፡፡


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ

64 ዳዊት አሰፋ

15 አዲሱ ሰይፉ – 12 አቤል አበበ – 5 ቶክ ጀምስ – 27 አንተነህ ገብረክርስቶስ

4 ጋብሬል አህመድ

21 ኤፍሬም አሻሞ – 80 ቢንያም በላይ – 8 ሰለሞን ገብረመድህን – 2 ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን

9 ፊሊፕ ዳውዚ

ተጠባባቂዎች

93 ዮሃንስ ሽኩር
98 ዳንኤል አድሃኖም
17 ስንታለም ተሻገር
6 አምሃ በለጠ
18 ታድዮስ ወልዴ
11 አብዱልከሪም ሀሰን
26 ዳኛቸው በቀለ


የመከላከያ አሰላለፍ

1 ጀማል ጣሰው

2 ሽመልስ ተገኝ – 16 አዲሱ ተስፋዬ – 3 ቴዎድሮስ በቀለ – 29 ሙሉቀን ደሳለኝ

10 ፍሬው ሰለሞን – 26 ኡጉታ ኦዶክ – 13 ሚካኤል ደስታ

19 ሳሙኤል ታዬ – 17 መሃመድ ናስር – 9 ሳሙኤል ሳሊሶ

ተጠባባቂዎች

22 ይድነቃቸው ኪዳኔ
7 ማራኪ ወርቁ
11 ሙጃኢድ መሃመድ
6 ታፈሰ ሰርካ
15 ቴዎድሮስ ታፈሰ
21 በሃይሉ ግርማ
20 ካርሎስ ዳምጠው


1 Comment

Leave a Reply