ታክቲካዊ ትንታኔ ፡ ደደቢት 2-0 ኤሌክትሪክ

ደደቢት በአዲሱ አሰልጣኙ ዮሃንስ ሳህሌ እየተመራ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል፡፡ የሶከር ኢትዮጵያው ሚልኪያስ አበራ ጨዋታውን ተመልክቶ ይህንን ታክቲካዊ ትንታኔ አዘጋጅቷል፡፡

የሊጉ 10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ጨዋታዎች በ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ቀጥለዋል፡፡ እሁድ በ8 ሰአት የቀድሞው የውድድሩ አሸናፊዎች ተገናኝተው በአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የሚመራው ደደቢት በጆኒ ስር የመጀመሪያ ድሉን በኤሌክትሪክ ላይ ተቀዳጅቷል፡፡ የአሰልጣኝ አጥናፉ ከበደ ቡድን ዘንድሮ አዘወትሮ እየተጠቀመበት ባለው የ 4-4-2 የተጫዋች የሜዳ ላይ አደራደር ጨዋታውን የጀመረ ሲሆን ሰማያዊዎቹ ደደቢቶች ደግሞ በሁለት የተከላካይ አማካይ የተዋቀረው የ 4-2-3-1 ፎርሜሽን ተግብረዋል፡፡

ምስል 1

የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ሒደት

ኤሌክትሪኮች በመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች ጎል ቢያስተናግዱም በማጥቃት የአጨዋወት ሒደት ላይ ተከላካዮች ወደ መሃለኛው የሜዳ ክፍል ቀርበው ሲጫወቱ ነበር፡፡ ከሁለቱ የኤሌክትሪክ አማካይ ተከላካዮች ዊልያም ኤሳድጆ ይበልጥ ወደ ፊት በመጠጋት አጥቂዎቹን ከአማካይና ከመስመር አማካዮቹ ጋር ለማገናኘት ሲሞክር ተስተውላል፡፡ በተጨማሪም አጥቂዎቹ ወደ መስመር በመለጠጥ በተጋጣሚ ሜዳ በማጥቃት ወረዳ ለቡድናቸው የጎንዮሽ ጥቅም (Width Advantage) ለማስገኘት ሲሞክሩ የሚፈጠረው ክፍተት ላይ እየተገኘ የቡድኑን የማጥቃት አጨዋወት (attacking phase) ሲረዳ ተስተውላል፡፡

የአሰልጣኝ ዮሃንስ ቡድን ጥንቃቄ የተስተዋለበት እንቅስቃሴ ሲያደርግ ይታያል፡፡ ተጫዋቾች በሚደረደሩባቸው መስመሮች መካከል የሚኖራቸውን ክፍተት በማጥበብ (compact ሆነው) እና በተከላካይ ተሰላፊዎች መካከል ባላቸው ከፍተኛ መናበብ ሥርኣት ቡድኑ የተጋጣሚ አጥቂዎችን ከጨዋታው ውጭ በማድረግ ጥሩ ተሳትፎ ነበራቸው፡፡ በቀን መስመር አማካይነት የተሰለፈው ሄኖክ ኢሳይያስ በቡድኑ የመከላከል እና ከማጥቃትና ወደ መከላከል በሚደረገው ሽግግር (Defendinge Transition) ላይ የነበረው ሚና በጨዋታው ከታዩ የቡድኑ ጠንካራ ጎኖች አንዱ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ተጫዋቱ በመከላከል አጨዋወት (Defendining Phase) በቀኙ ክፍል ወደ ኋላ በማፈግፈግ ከሁለቱ የተከላካይ ማካዮች ጎን በመገኘት መስመሩ ላይ ጥንካሬን ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም ሻይቡ ጋብሬል ይበልጥ ወደ ግራ አዘንብሎ በሜዳው ወርድ የሚኖረውን ቦታ እንዲሸፍን ያግዛል፡፡

የቡድኑ ተጫዋቾች ተቀራርበው በመጫወታቸው ቡድን የሚፈጠረውን የመልሶ ማጥቃት አጨዋወት (Counter – Attaking) ተጋላጭ እንዳይሆን አግዛቸዋል፡፡

የመብራት ሀይል የመስመር አማካዮች የፊትለፊት ሩጫ (Overlaping movement) ብዙም ተጋጣሚ ላይ ጫና የሚፈጥር ያልነበረበት ምክንያትም ከደደቢት የመስመር አማካዮች አፈግፍጎ መከላከል ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ቢኖለውም የቡድኑ (የመብራት) የመስመር አማማካዮችም ከመስመሩ ይልቅ ወደ መሃል እየገቡ አብዛኛው ግዜያቸውን ማሰለፋቸውም ሌላው አይነተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተ መንስኤ ነበር፡፡ በ40ኛው ደቂቃ አከባቢ አወት overlap በማደረግ ከፈጠረው ተሻጋሪ ኳስ ከተገኘው የጎል ሙከራ ውጭ አስጊ ጫና በደደቢት መስመሮች ላይ አልተስተዋለም፡፡

ምስል 2

Dedebit 2-0 Electric (2)

2ኛው አጋማሽ

ደደቢቶች በዚህኛው ጨዋታ ክፍለግዜ ከመጀመርያው አጋማሽ ብዙም ተለወጠ የአጨዋወት ሥልት ይዘው አልቀረቡም፡፡ በተጫዋቾች ለውጥ ከተደረገው የቦታ ቅያሪ ውጭ ቡድኑ ስጫወትበት የነበረውን ዘዴ ቀጥሎበታል፡፡ ሽመክት ጉግሳ ከዳዊት ጀርባ በመሆን አማካዩን እና አጥቂ ክፍሉን link ለማድግ የሞከረ ሲሆን በመስመር ተከላካዮች እና በመሃል ተከላካዮች መካከል (through the channels) በመገኘት የማጥቃት ማዕዘናትን ሲያሰፋ ነበር፡፡ ደደቢት ስኬታማ የተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ ተጨማሪ ጎል ሊያስቆጥርም ችሏል፡፡ በ74ኛው ደቂቃ አካባቢም በረከትን በሳሚ ሳኑሚ ተክቶ ዳዊትን ከማጥቃት ክልሉ ወደ ግራ መስመር አማካይነት በመለወጥ 9 የአጥቂነት ሚና ወሰደ፡፡ በ72ኛው ደቂቃም ዳዊትን በሳምሶን ጥላሁን በመተካት ሽመክት ወደ ግራው አዘንብሎ ሳምሶን ከበረከት ጀርባ link የማድረጉን ስራ ቀጠለ፡፡ ይህም በ86ኛው ደቂቃ ላይ ለተገኘው 2ኛ ጎል ምክንያት ሆኗል፡፡ በመልሶ ማጥቃት የተገኘችዋን ኳስ ሳምሶን ለ በረከት በረጅሙ አሻግሮለት 9 በእርጋታ ከተቆጣጠራት በኋላ ወደ ጎልነት ቀይሯታል፡፡

 

የኤሌክትሪክ አወዛጋቢ የተጫዋቾች ሚና

የአሰልጣኝ አጥናፉ ቡድን ከእረፍት መልስ ወንድሜነህ እና ዮርዳኖስን በማስገባት የበለጠ የማጥቃት ጫና ለመፍጠር ሞክሯል፡፡ አዲስን ወደ ኋላ በመመለስ ከዊሊያም ጋር የተከላካይ አማካይነትን ሚና እንዲጫወት ያደdረገ ሲሆን ቀድሞ ከነበረው የመሀል ሜዳ የተጫዋቾች አደራደር ቅርጽ በተለየም የ box midfield መዋቅር ያዘ፡፡ ይህም የቡድኑን አጨዋወት ወደ 4-2-2-2 ፎርሜሽን የቀየረ ሂደት ነበር፡፡ ሁኔታው ቡድኑን ይበልጥ በመስመሮች ላይ ክፍተትን የሚፈጥርበት ቢሆንም ተጋጣሚው ያንን ሰፊ space መጠቀም አለመቻሉ ከጨዋታው አስገራሚ ሁነቶች አንዱ ነበር፡፡ ከጨዋታው መጀመሪያ አንስቶ የኤሌክትሪኩ አዲስ ነጋሽ ሚና ግራ አጋቢ ነበር፡፡ በ4-4-2 በመስመር አማካይነት ቢገባም
አብዛኛውን የጨወታ ጊዜ ያሳለፈው ግን በመሃከለኛው የሜዳ ክፍል ነው፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ ደደቢት ያንን ክፍተት አለመጠቀሙ በጀው እንጂ ጥሎት የሚሄደው ቦታ ለተጋጣሚ ቡድን የመስመር የማጥቃት እንቅስቃሴ አመቺ ነበር፡፡

ምስል 3

 

Dedebit 2-0 Electric (3)

ያጋሩ