ሊግ ዋንጫ ፍጻሜ : ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መከላከያ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-1 (4-3) መከላከያ
58′ አዳነ ግርማ | 14′ ሳሙኤል ሳሊሶ


image

ደጉ ደበበ ዋንጫውን ከፍ አድርጎ አንስቷል፡፡ ፈረሰኞቹም የሁለትዮሽ ዋንጫ ባለቤት መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

– ደጋፊው ከተጨዋቾቹ ጋር በመሆን አስገራሚ የደስታ አገላለፆች ሲያሳዩ እየተመለከትን እንገኛለን፡፡

5ኛ ምት – ቴዎድሮስ በቀለ ሳተ፡፡ በመለያ ምቶቹ ቅዱስ ጊዮርጊስ 4-3 አሸንፎ ቻምፒዮን ሆኗል፡፡ ዘሪሁን ታደለ ሁለት ኳሶች በማዳን የጨዋታው ጀግና ሆኗለል፡፡

4ኛ ምት – ምንተስኖት አዳነ አስቆጠረ፡፡ 3-4
4ኛ ምት – ሳሙኤል ሳሊሶ አስቆጠረ፡፡ 3-3

3ኛ ምት – ዳዋ ሁቴሳ አስቆጠረ፡፡ 2-3
3ኛ ምት – ቴዎድሮስ ታፈሰ ሳተ፡፡ 2-2

2ኛ ምት – ሳላዲን ሰኢድ አስቀጠረ፡፡ 2-2
2ኛ ምት – በሃይሉ ግርማ አስቆጠረ፡፡ 2-1

1ኛ ምት – አበባው ቡታቆ ለጊዮርጊስ አስቆጠረ፡፡ 1-1
1ኛ ምት – መሃመድ ናስር ለመከላከያ አስቆጠረ፡፡ 1-0


ተጠናቀቀ
ጨዋታው 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ አሸናፊው በመለያ ምቶች ይለያል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
በሃይሉ አሰፋ ወጥቶ አበባው ቡታቆ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
ፍሬው ሰለሞን ፣ ሚካኤል ደስታ እና ጀማል ጣሰው ወጥተው በሃይሉ ግርማ ፣ ቴዎድሮስ ታፈሰ እና ይድነቃቸው ኪዳኔ ገብተዋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

ቀይ ካርድ
89′
አስቻለው ታመነ በፍሬው ላይ በሰራው ጥፋት በሁለተኛ ቢጫ ከሜዳ ተወግዷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
85′
ዘካርያስ ቱጂ ወጥቶ ዳዋ ሁቴሳ ገብቷል፡፡

85′ በሁለቱም በኩል በፈጣን እንቅስቃሴ ወደ ጎል ለመቅረብ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

77′ ሳሙኤል ሳሊሶ በግሩም እንቅስቃሴ ከርቀት የመታው ኳስ የግቡ አግዳሚ መልሶበታል፡፡ ድንቅ ሙከራ!

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
73′
ናትናኤል ዘለቀ ወጥቶ ተስፋዬ አለባቸው ገብቷል፡፡

72′ ፍሬው ሰለሞን አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ሳሙኤል ሳሊሶ ሞክሮ ዘሪሁን አድኖበታል፡፡

ቢጫ ካርድ
67′
ናትናኤል ዘለቀ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

60′ በስቴዲዮሙ የሚገኙ በርካታ የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች ቡድናቸውን በዜማ እያነቃቁ ይገኛሉ፡፡

ጎልልል!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ
አዳነ ግርማ የፍፁም ቅጣት ምቱን ወደ ግብነት ለውጦታል፡፡

ፍጹም ቅጣት ምት
57′
ሳጥን ውስጥ መሃመድ ናስር ኳስ በእጅ በመንካቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የፍጹም ቅጣት ምት አግኝቷል፡፡

50′ ጊዮርጊሶች ተጭነው እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡ ሳላዲን ያገኘውን መልካም የማግባት አጋጣሚ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

48′ ሜዳው ውሃ የቋጠረ በመሆኑ ኢንተርናሽናል ዳኛ በምለክ በተደጋጋሚ እየወደቁ ይገኛሉ፡፡ ተመልካቹም በሁኔታው ዘና እያለ ይገኛል፡፡

ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በመከላከያ መሪነት ተጠናቋል፡፡ አዳነ ግርማ ፊሽካ ከተነፋ በኋላ ከዳኛ ጋር በገባው ውዝግብ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
45+1′
ምንተስኖት አዳነ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

ቢጫ ካርድ
44′
መሃሪ መና የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

40′ ፈረሰኞቹ አሁንም በምተስኖት አማካኝነት የፈጠሩትን ግልፅ የማግባት አጋጣሚ ጀማል ጣሰው አድኖታል፡፡

39′ በኃይሉ አሰፋ ከመስመር ያሻገረለትን ኳስ አዳነ ግርማ በግንባሩ ገጭቶ ጀማል አወጣበት፡፡ ግሩም ሙከራ!

38′ ፈረሰኞቹ የጦረኞቹን ፈጣን እንቅስቃሴ መግታት የተሳናቸው ይመስላል፡፡ የሀይል አጨዋወት እየተጠቀሙም ይገኛሉ፡፡

35′ መሃመድ ናስር በድንቅ ሁኔታ አንድ ሁለት ተቀባብሎ በመግባት የመታውን ኳስ ዘሪሁን እንደምንም አውጥቶታል፡፡

28′ ፈረሰኞቹ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ተደጋጋሚ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በሳላዲን ፣ ናትናኤል እና መሃሪ አማካኝነትም ሙከራዎች አድርገዋል፡፡

23′ በጥሩ የኳስ ቅብብል ወደ ጎል የደረሰውን ኳስ ፍሬው ሰለሞን አምክኖታል፡፡ የሚያስቆጭ የጎል አጋጣሚ!

22′ በፈጣን እንቅስቃሴ የጨዋታ ብልጫ የወሰዱት መከላከያዎች ተጨማሪ ጎል ለማግኘት ተጭነው እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡

ጎልልል!!!! መከላከያ
14′ ሳሙኤል ሳሊሶ ከ20 ሜትር ርቀት ራሱ ላይ የተሰራውን ፋውል ተከትሎ የተገኘውን ቅጣት ምት በግሩም ሁኔታ ወደ ጎልነት ቀይሮታል፡፡

ቢጫ ካርድ
16′
ደጉ እና አስቻለው የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል፡፡

ቢጫ ካርድ
8′
ሽመልስ ተገኝ የጨዋታውን የመጀመርያ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

5′ አዳነ ግርማ የጀማል ጣሰውን ስህተት ተጠቅሞ በግራ እግሩ ከመሬት ጋር አስታኮ የመታው ኳስ ለጥቂት ወጣ፡፡ የጨዋታው የመጀመርያ ጠንካራ ሙከራ!

ተጀመረ!
በመከላከያ ጀማሪነት ጨዋታው ተጀመረ፡፡

09:18 ሁለቱም ቡድኖች የዕለቱን እንግዶች የሆኑት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት እና ስራ አስፈጻሚ አባላት በመተዋወቅ ላይ ይገኛሉ፡፡


የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

22 ዘሪሁን ታደለ

15 አስቻለው ታመነ – ደጉ ደበበ (አምበል) – 5 አይዛክ ኢዜንዴ – 3 መሃሪ መና

23 ምንተስኖት አዳነ – 26 ናትናኤል ዘለቀ

20 ዘካርያስ ቱጂ –19 አዳነ ግርማ – 7 በሃይሉ አሰፋ

10 ሳላዲን ሰኢድ

ተጠባባቂዎች
1ፍሬው ጌትነት
2 ፍሬዘር ካሳ
4 አበባው ቡታቆ
6 አሉላ ግርማ
11ዳዋ ሁቴሳ
14 አለማየሁ ሙለታ
18 አቡበከር ሳኒ


የመከላከያ አሰላለፍ
1 ጀማል ጣሰው

2 ሽመልስ ተገኝ – 16 አዲሱ ተስፋዬ – 3 ቴዎድሮስ በቀለ – 29 ሙሉቀን ደሳለኝ

10 ፍሬው ሰለሞን – 26 ኡጉታ ኦዶክ – 13 ሚካኤል ደስታ

19 ሳሙኤል ታዬ – 17 መሃመድ ናስር – 9 ሳሙኤል ሳሊሶ

ተጠባባቂዎች

22 ይድነቃቸው ኪዳኔ
7 ማራኪ ወርቁ
11 ሙጃኢድ መሃመድ
6 ታፈሰ ሰርካ
15 ቴዎድሮስ ታፈሰ
21 በሃይሉ ግርማ
20 ካርሎስ ዳምጠው

1 Comment

  1. Almost all players of Saint George have taken yellow card. Why? Do they have moral to talk about moral and sport discipline? Most have payed in the premier league above 15 years. Shame

Leave a Reply