አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ እና መከላከያ ተለያዩ

መከላከያ እና አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለመለያየት ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

ከ2004 ጀምሮ በመከላከያ የቆዩት አስልጣኝ ገብረመድህን በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ክለቡን እንደሚለቁ ለክለቡ አሳውቀው የነበረ ሲሆን በዛሬው እለት የተካሄደው የጥሎ ማለፍ ፍጻሜ ጨዋታ በመከላከያ አሰልጣኝነታቸው የመጨረሻ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ተረክበው በመስራት ላይ የሚገኙት አሰልጣኝ ገብረመድህን በቀጣዩ አመት በሌላ የፕሪሚየር ሊግ ክለብ አሰልጣኝነት እንደሚመለሱ ለሶከር ኢትዮጵያ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

” በቀጣዩ አመት በክለብ አሰልጣኝነት መመለሴ አይቀርም፡፡ አሁን የምገኘው ድርድር ላይ በመሆኑ የትኛው ክለብ እንደሆነ መናገር አልችልም” ብለዋል፡፡

አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ በትራንስ ኢትዮጵያ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ኢትዮጵያ መድን ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ደደቢት አሰልጣኝነት ቢያሳልፉም በዋንጫ የታጀበ ጊዜ ያሳለፉት በመከላከያ ነው፡፡ በመከላከያ ሁለት ጊዜ የጥሎ ማለፍ አሸናፊ ሲሆኑ አንድ ጊዜ ለፍጻሜ ደርሰው በቅዱስ ጊዮርጊስ ተሸንፈው ዋንጫ አጥተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *