ዘሪሁን ታደለ እና አዳነ ግርማ ስለ ትላንቱ ድል ይናገራሉ

ፈረሰኞቹ ጦሩን በመለያ ምት 4-3 በማሸነፍ የሁለትዮሽ ዋንጫን ማሸነፍ ችለዋል፡፡ በጨዋታው ላይ ቅዱስ ጊዮርጊሰን ወደ ጨዋታው የመለሰችውን ግብ በፍፁም ቅጣት ምት ያስቆጠረው አዳነ ግርማ እና በዕለቱ ሁለት ፍፁም ቅጣት ምቶችን ያዳነው ግብ ጠባቂው ዘሪሁን ታደለ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

PicsArt_1467958950559

“ጊዮርጊስ ውስጥ ምንጊዜም የተሸናፊነት መንፈስ የለም” አዳነ ግርማ

ጊዮርጊስ ሁሌም የተሸናፊነት ስሜት የለንም፡፡ ሁሌም በምንመራ ሰዓት ሁላችንም መቶ በመቶ ነው ለማሸነፍ የምንጠረው፡፡ በመጀመሪያ አጋማሽ ተዘናግተን ነበር፡፡ እነሱ ጥሩ ነበሩ፡፡ በሁለተኛው 45 በጥሩ እንቅስቃሴ እና መልሶ ማጥቃት እየተጫወትን ግብ ማስቆጠር ችለናል፡፡ ብዙ ማግባት የሚገባን ግቦች ነበሩ፡፡ የጀማልም ጥሩነት ነው ግብ እንዳናስቆጥር ያደረገን፡፡ በአጠቃላይ በጣም ደስ ብሎኞል፡፡

ሁሌም የጊዮርጊስ ደጋፊ ከኔ ግብ ይጠብቃል፡፡ ግብ ማግባት ደግሞ ስራዬ ነው፡፡ ስራዬን አክብሬ ስለምሰራ ነው ሁሌም ወጥ አቋም ላይ የምገኘው፡፡ ይህ የውድድር ዓመት ለኔ ትልቅ ነበር፡፡ ለምን ቢባል ሁለት ዋንጫ ያገኘሁበት ነው፡፡ ብዙ ግቦችን ለጊዮርጊስ ማግባት ችያለው፡፡ በስነ ስርዓት እና በትክክለኛው መንገድ ስራዬን እየሰራው እገኛለው፡፡

PicsArt_1467958877296

“እኔ እራሴ ወደ መለያ ምት እንድንደርስ በጣም ፈልጌ ነበር” ዘሪሁን ታደለ

የጊዮርጊስ ሻምፒዮን መሆኑ ዋነኛ ነገር ህብረታችን ነው፡፡ ያለን አንድነት እና ፍቅር ነው ዋንጫ እንድናነሳ ያደረገን፡፡ ፍፁም ቅጣት ምቶችን ሁልጊዜ አንለማመዳለን፡፡ ከአሰልጣኞቼ እና ተጫዋቾች ጋር ፍፁም ቅጣት ምት ላይ ልምምድ ስለማደርግ ለእኔ በጣም ቀላል ነው፡፡ እኔ ራሴ ወደ መለያ ምት እንድንደርስ በጣም ፈልጌ ነበር፡፡ ነገር ግን በጨዋታ ማሸነፍ የምንችልባቸውንም ብዙ አጋጣሚዎች አልተጠቀምንባቸውም፡፡

Leave a Reply