ወደ ከፍተኛ ሊግ ለማለፍ በ16 ክለቦች መካከል የሚካሄደው የ2008 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር በባቱ (ዝዋይ) ከተማ እዲካሄድ ከውሳኔ ተደርሷል፡፡
ወድድሩ ከሀምሌ 16 እስከ ነሀሴ 2 የሚካሄድ ሲሆን በዋነኝነት በሼር ኢትዮጵያ ስታድየም ላይ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
የብሄራዊ ሊጉ የዞኖች ውድድር ሰኔ 26 ቀን 2008 ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ወደ ማጠቃለያው ዙር ያለፉት 16 ክለቦችም ተለይተው ታውቀዋል፡፡
16ቱ ክለቦች
ከየዞናቸው በ1ኝነት ያለፉ
ቡታጅራ ከተማ ፣ ወልቂጤ ከተማ ፣ አማራ ፖሊስ ፣ ደሴ ከተማ ፣ ከፋ ቡና ፣ አምባሪቾ ፣ መተሃራ ስኳር
ከየዞናቸው በ2ኝነት ያለፉ
ለገጣፎ ፣ አራዳ ፣ ዳባት ከተማ ፣ ሰሎዳ አድዋ ፣ ሚዛን አማን ፣ ዲላ ከተማ ፣ ሞጆ ከተማ
በጥሩ 3ኝነት ያለፉ
ወሊሶ ከተማ (በአማካይ በጨዋታ 1.9 ነጥብ በማስመዝገብ) ፣ ሽረ እንዳስላሴ ( በአማካይ በጨዋታ 1.8 ነጥብ በማስመዝገብ)
ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዴት ያልፋሉ?
ከከፍተኛ ሊጉ የሚወርዱ 4 ክለቦችን ተክተው ከብሄራዊ ሊጉ የሚያልፉት 6 ክለቦች ናቸው፡፡ በማጠቃለያ ውድድሩ የግማሽ ፍጻሜውን የሚቀላቀሉ 4 ክለቦች በቀጥታ ወደ ከፍተኛ ሊጉ ሲያልፉ በሩብ ፍፃሜ የሚወድቁት 4 ክለቦች እርስ በእርስ ተጫውተው አሸናፊ የሚሆኑ 2 ክለቦች ወደ ከፍተኛ ሊግ ያልፋሉ፡፡
6 ክለቦች የሚያልፉበት ምክንያት
የቀጣዩ አመት ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊዎች ቁጥር ወደ 16 ከፍ የሚል በመሆኑ በሚወርዱት 2 ክለቦች ምትክ ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ የሚያልፉት ክለቦች 4 ይሆናሉ፡፡ ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የሚያድጉት 4 ፣ ወደ ብሄራዊ ሊግ የሚወርዱት 4 (በአጠቃላይ 8 ቡድኖች) በመሆናቸው ከፕሪሚየር ሊግ የወረዱ 2 ክለቦች እና ከብሄራዊ ሊግ የሚያድጉ 6 ክለቦች (በአጠቃላይ 8 ክለቦች) የወጡትን ክለቦች ይተካሉ፡፡