የኢትየጵያ U-17 ፕሪሚየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ቅዳሜ ይጀመራል

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ በአዳማ ከተማ አስተናጋጅነት በመጪው ቅዳሜ ይጀመራል፡፡ 10 ክለቦች የሚካፈሉበት የማጠቃለያ ውድድር ለ2ኛ ተከታታይ አመት በአዳማ የሚካሄድ ሲሆን እስከ ሐምሌ 23 ድረስ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በሁለት ዞኖች ተከፍሎ በተካሄደው የዘንድሮው የሊግ ውድድር ከመካለከኛው ዞን 6 ክለቦች ፣ ከ ደቡብ-ምስራቅ ዞን ደግሞ 4 ክለቦች ወደ ማጠቃለያው ውድድር ያለፉ ሲሆን አርብ የእጣ ማውጣት ስነስርአቱ በአዳማ ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በውድድሩ ደንብ መሰረት ክለቦቹ ይዘው ባጠናቀቁት ደረጃ መሰረት የምድብ ድልድሉ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ከመካከለኛው ዞን ያለፉ

ደደቢት ፣ ሐረር ሲቲ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ መከላከያ እና አዲስ አበባ ከተማ

ከደቡብ-ምስራቅ ዞን ያለፉ

ሀዋሳ ከተማ ፣ ወላይታ ድቻ ፣ ሲዳማ ቡና እና አዳማ ከተማ

Leave a Reply