ደደቢት ዮሃንስ ሳህሌን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ለማድረግ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡
አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በግንቦት ወር ከብሄራዊ ቡድኑ ከተሰናበቱ በኋላ እረፍት ላይ የነበሩ ሲሆን ስማቸው ከተለያዩ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ስራ ጋር ተያይዞ ሲነሳ ቆይቶ ነበር፡፡
የአሰልጣኝ ዮሃንስ እና ደደቢት ስምምነት በክለቡ ይፋ ያልተደረገ ሲሆን የኮንትራቱ ዝርዝር በቅርብ ቀናት ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዮሃንስ ሳህሌ ለ3ኛ ጊዜ ወደ ደደቢት የሚመለሱ ሲሆን በ2003 ለአጭር ጊዜ በቴክኒክ ዳይሬክተርነት ሲሰሩ ለሁለተኛ ጊዜ በተመለሱበት 2007 ደግሞ ለ6 ወራት ክለቡን በአሰልጣኝነት መርተዋል፡፡
የዮሃንስ መመለስ በብሄራዊ ቡድኑ የአሰልጣኙ እምነትን ያገኙ ተጫዋቾች ክለቡን እንዲቀላቀሉ በር ይከፍታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ከላይ ያለው ምስል አሰልጣኝ ዮሃንስ ከ1 አመት ከ6 ወር በፊት የደደቢት አሰልጣኝ በሆኑበት ወቅት የተነሱት ነው፡፡