መብራት ኃይል ከአስቸጋሪ ጊዜያት ለመውጣት መነሻ የምትሆነውን ድል ቅዳሜ በመድን ላይ ሲያስመዘግብ ከተጠባባቂ ወንበር ተነስቶ ወሳኝ ሚና የተወጣው የመስመር አማካዩ አብዱልከሪም ሀሰን በድሉ መደሰቱን ለሀት-ትሪክ ጋዜጣ ተናግሯል፡፡
‹‹ ድሉ ለሳምንታት ከቆየንበት የደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ያላቀቀን በመሆኑ ለቀጣይ ጨዋዎች ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥርልናል፡፡ ጨዋታው ከብዶን ነበር፡፡ በተለይ በመጀመርያው አጋማሽ ጥሩ መንቀሳቀስ አልቻልንም ፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ላሳየነው መሻሻል የተደረጉት የተጫዋቾች ቅያሪ ጠቅሞናል፡፡ ..
አብዱልከሪም ሀሰን በ2004 ቅዱስ ጊዮርጊስን ለቆ መብራት ኃይልን ሲቀላቀል በፈረሰኞቹ ቤት ያጣውን የቀቋሚ ተሰላፊነት እድል ለማግኘት ቢሆንም በቀዮቹም ቤት በርካታ ጨዋታዎችን ከተጠባባቂ ወንበር ሆኖ ለመጀመር ተገዷል፡፡ ያም ሆኖ ባለ ተሰጥኦው የመስመር አማካይ ተጠባባቂ መሆኑ እንደማያሳስበው ተናግሯል፡፡
‹‹ በርካታ ጨዋታዎች ላይ ተጠባባቂ መሆኔ ደስተኛ ሊያደርገኝ አይችልም፡፡ ነገር ግን የእኔ ተጠባባቂ መሆን ከቡድኑ በወራጅ ቀጠና ውስጥ መገኘት የበለጠ አያሳስበኝም፡፡ አሁን ዋናው ትኩረቴ መብራት ኃይል ከወራጅ ቀጠናው እንዲርቅ መርዳት ብቻ ነው፡፡ ሁልጊዜም ጠንክሬ ስለምሰራ ወደ ቋሚ አሰላለፉ እንደምመለስ እምነት አለኝ፡፡ ›› ሲል የመብራት ኃይል ወቅታዊ ሁኔታ እንደሚያሳስበው ገልጧል፡፡
{jcomments on}