ኢትዮጵያ በፊፋ የሃገራት ደረጃ 7 ደረጃዎችን አሽቆልቁላለች

የአለም አቀፉ እግርኳስ አስተዳዳሪ አካል /ፊፋ/ የሃገራት ወርሃዊ ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያ ካለፈው ወር 7 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል 132ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

በወር ውስጥ አንድ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ያደረገችው ኢትዮጵያ ባለፉት 2 ወራት በ125ኛ ደረጃ ላይ ረግታ የቆየች ሲሆን በዚህ ወር 269.5 ነጥብ በመሰብሰብና 7 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል 132ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ከአፍሪካ ሃገራት ደግሞ 41ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ከአፍሪካ ሃገራት መካከል አልጄርያ ከአለም 32ኛ ደረጃ በመያዝ አሁንም ቀዳሚነቷን ስታስጠብቅ ኮትዲቯር 35ኛ ደረጃ በመያዝ ሁለተኛ ነች፡፡ ጋና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ሴኔጋል ፣ ግብጽ ፣ ቱኒዚያ ፣ ካሜሩን ፣ ሞሮኮ ፣ ኮንጎ ዲሪ እና ማሊ እስከ 10ኛ ደረጃ የተቀመጡ ሃገራት ናቸው፡፡

የአለም ሃገራት ደረጃን የኮፓ አሜሪካ የፍጸሜ ተፋላሚዋ አርንቲና መምራቷን ስትቀጥል ቤልጅየም ፣ ኮሉምቢያ ፣ ጀርመን ፣ ቺሊ ፣ ፖርቱጋል ፣ ፈረንሳይ ፣ ስፔን ፣ ብራዚል እና ጣልያን ተከታዮቹ ደረጃዎችን ይዘዋል፡፡

Leave a Reply