በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ትላንት ሊደረግ የነበረው የወራቤ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ጨዋታ በጣለው ዝናብ ምክንያት ለዛሬ 04:00 ቢተላለፍም ሜዳው ባለመድረቁ ጨዋታው ሳይደረግ ቀርቷል፡፡ ጨዋታውም ዛሬ ተወስኖ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ከደቂቃዎች በፊት ማስነበባችን ይታወቃል፡፡
ከደቂቃዎች በፊት በደረሰን መረጃ ደግሞ የወራቤ ሜዳ ሁኔታ ጨዋታውን ለማድረግ የማያስችል በመሆኑ ጨዋታው በሆሳዕና እንዲደረግ የተወሰነ ሲሆን ነገ 08:00 ላይ ይካሄዳል፡፡
ጨዋታው ነገ መደረጉ ሁለቱ ክለቦች ከጅማ አባ ቡና እና ጂንካ ከተማ ጋር ሰኞ እንዲያደርጉ የወጣላቸው ተስተካካይ ጨዋታ የቀን ሽግሽግ እንዲደረግ ሊያስገድድ ይችላል፡፡
ሁለቱ ክለቦች በ3 ነጥቦች ልዩነት 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሲሆን ይህን ጨዋታ ሳይጨምር አዲስ አበባ ከተማ 3 ፣ ወራቤ ከተማ ደግሞ 1 ተስተካካይ ጨዋታ ይቀራቸዋል፡፡