በከፍተኛ ሊጉ ትላንት ያልተደረጉት 3 ጨዋታዎች መቼ እና የት እንደሚደረጉ ታወቋል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ትላንት ሊደረጉ የነበሩት 3 ጨዋታዎች ሳይካሄዱ በመቅረታቸው ተለዋጭ ቀናት እና ሜዳዎች በማመቻቸት ከነገ ጀምሮ እስከ ሰኞ እንዲካሄዱ ተወስኗል፡፡

ባህርዳር ላይ በባህርዳር ከተማ እና መቀለ ከተማ መካከል ሊካሄድ የነበረው ጨዋታ እሁድ 10:00 ላይ በአበበ ቢቂላ እንደዲደረግ ተወስኗል፡፡

በተመሳሳይ ባህርዳር ላይ ሊካሄድ የነበረው የአማራ ውሃ ስራ እና ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ጨዋታ ሰኞ 05:00 ላይ በአዳማ አበበ ቢቂላ ይደረጋል፡፡ ጨዋታው በአበበ ቢቂላ ስቲድየም ሊደረግ ታስቦ የነበረ ቢሆንም ኢትዮጵያ ውሃ ስራ የአአ ክለብ በመሆኑ ጨዋታው ወደ አበበ ቢቂላ ስታድየም ተሸጋግሯል፡፡

በምድብ ለ ትላንት በዝናብ ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቶ ዛሬም መደረግ ያልቻለው የወራቤ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ጨዋታ ነገ 08:00 ላይ በሆሳዕና አቢዮ አርሳሞ ስታድየም እንዲደረግ ተወስኗል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *