ንግድ ባንክ በክረምቱ ከግዢ ይልቅ ተጫዋቾችን ከተስፋ ቡድን በማሳደግ ላይ አተኩሯል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተለመደው የክለቡ አካሄድ ለየት ባለ መልኩ በክረምቱ ወደ ገብያ ከመውጣት ይልቅ ከተስፋ ቡድኑ ተጫዋቾችን ማሳደግ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡

በዚህ ሳምንት በስብሰባ ተጠምዶ ያሳለፈው የንግድ ባንክ ቦርድ ደካማ አቋም አሳይተዋል ያላቸውን ተጫዋቾችን ለማሰናበት የወሰነ ሲሆን 7 ተጫዋቾች ከተስፋ እንዲያድጉም ተደርጓል፡፡

PicsArt_1468589540771

ከክለቡ ጋር የነበራቸው የውል ዘመን መጠናቀቁን ተከትሎ ማራዘምያ ያልቀረበላቸውን ጨምሮ 7 ተጫዋቾች ከክለቡ እንደሚለቁ ተረጋግጧል፡፡ ናይጄርያዊው ፊሊፕ ዳውዚ ፣ ግብ ጠባቂዎቹ ዮሃንስ ሽኩር እና ዳዊት አሰፋ እንዲሁም አማካዮቹ ሰለሞን ገብረመድህን ፣  አብዱልከሪም ሀሰን ፣ ሲሳይ ቶሊ ፣ ስንታለም ተሻገር ፣ ናኦድ ሙባረክ እና እያሱ መኩርያ ከክለቡ የሚለቁ ሲሆን በክለቡ ታግዶ የሚገኘው ቢንያም አሰፋ ጉዳይ በቅርቡ እልባት እንደሚያገኝ ይጠበቃል፡፡

ክለቡን ከለቀቁት ተጫዋቾች መካከል አብዱልከሪም ሀሰን ለኢትዮጵያ ቡና ለመፈረም ከስምምነት መድረሱ ሲነገር ፊሊፕ ዳውዚም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ስሙ ተያይዟል፡፡ ፊሊፕ ከኢትዮጵያ ውጪ ካሉ ክለቦች ጋርም ግንኙነት መጀመሩ ተሰምቷል፡፡

PicsArt_1468589486138

ያለፉት አመታት ዋንኛ የዝውውር መስኮት ተዋናይ የነበረው ንግድ ባንክ ዘንድሮ ለዝውውር ከፍተኛ ገንዘብ የሚያወጣ አይመስልም፡፡ በለቀቁት ተጫዋቾች ምትክ የውድድር ዘመኑን በቻምፒዮንነት ካጠናቀቀው የንግድ ባንክ ተስፋ ቡድን ከማሳደጉ ውጪ ገብያ ወጥቶ የሚያስፈርማቸው ተጫዋቾች ከ3 እንደማይዘሉ ታውቋል፡፡

1 Comment

Leave a Reply