ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር እጣ ማውጣት ስነስርአት ዛሬ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ከሀምሌ 9 እስከ 23 በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ይደረጋል፡፡ የውድድሩ እጣ ማውጣት ስነስርአት እና ቅድመ ውድድር ውይይትም ዛሬ በአዳማ ምክርቤት አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በእለቱ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ አሊሚራ መሃመድ ፣ የውድድር እና ስነስርአት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ገብረስላሴ እና የአዳማ ከተማ ክለብ ፕሬዝዳንት አቶ አንበሴ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በውድድሩ ደንብ ፣ የእድሜ ጉዳይ አሳሳቢነት ፣ በዝግጅት ፣ ስፖርታዊ ጨዋነት እና የቀጣይ አመት ውድድር ዙርያ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡

በእድሜ ጉዳይ ላይ አሁን የሚሰራ ስራ እንደማይኖር ተጠቅሶ በቀጣይ አመት በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ የማጣራት ስራ እንደሚሰራ ተጠቅሷል፡፡

ለኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን የተመረጡ ተጫዋቾች ወደ ክለቦቻቸው ተመልሰው እንዲጫወቱ ተወስኗል፡፡

የውድድሩ ፎርማትን በተመለከተ በቀጣዩ የውድድር ዘመን የዞኖች ውድድር እንደማይኖር ተጠቅሶ በወጥነት የዙር ውድድር እንደሚሆንና የተሳታፊዎች ቁጥር እንደሚጨምርም ተገልጿል፡፡

ዛሬ የወጣው የምድብ ድልድል እና የመጀመርያ ቀን ጨዋታዎች

ምድብ ሀ

ሀዋሳ ከተማ ፣ ሐረር ሲቲ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ አዲስ አበባ ከተማ

ምድብ ለ

ደደቢት ፣ አዳማ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ንገድ ባንክ ፣ ወላይታ ድቻ ፣ መከላከያ

የመጀመርያ ጨዋታዎች

ቅዳሜ ሐምሌ 9 ቀን 2008

08:00 አዳማ ከተማ ከ መከላከያ

10:00 ደደቢት ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

– አራፊ ክለብ – ወላይታ ድቻ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *