አቤል ማሞ ከመከላከያ ጋር ድርድር ላይ ይገኛል ፤ ጀማል እና ፍሬው የመውጫውን በር እየተመለከቱ ነው

መከላከያ ኮንትራታቸውን የጨረሱ አብዛኛዎቹ ተጫዋቾችን ውል በማደስ ላይ ሲሆን ጀማል ጣሰው እና ፍሬው ሰለሞን ያቀረቡት የውል ማደሻ ሂሳብ ከፍተኛ በመሆኑ ከስምምነት መድረስ አልቻሉም፡፡

ፍሬው ሰለሞን ከቅዱሰ ጊዮርጊስ ዝውውር ጋር ስሙ መያያዙ ሲቀጥል በመከላከያ የመቆየቱ ጉዳይም አጠራጣሪ ሆኗል፡፡

ጀማል ጣሰው እና ሙሉአለም ጥላሁንም ከክለቡ ጋር ሊለያዩ የሚችሉ ሌሎች ተጫዋቾች ናቸው፡፡ በተለይም የአቤል ማሞ በመከላከያ መፈለግ ጀማል የመውጫውን በር እንዲመለከት ያደርገዋል ተብሏል፡፡

PicsArt_1468657260802

ከተስፋ ቡድኑ በቢጫ ቴሴራ ለዋናው ቡድን ሲጫወቱ የነበሩት አጥቂው አቤል ከበደ እና ተከላካዩ ሙጃሂድ መሃመድ ወደ ዋናው ቡድን ሙሉ ለሙሉ ሲያድጉ የተሻ ግዛው እና አወል አብደላ ወደ መከላከያ ለመመለስ እየተደራደሩ ይገኛሉ፡፡ የብሄራዊ ቡድኑ ግብ ጠባቂ አቤል ማሞም ከክለቡ ጋር እየተደራደረ የሚገኝ ተጫዋች ነው፡፡

ከሶስቱ ተጫዋቾች ዝውውር ባሻገር መከላከያ ከጉዳት በሚመለሱ ተጫዋቾቹ ላይ ተስፋውን የጣለ ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር አመት ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ያሳዩት ቴዎድሮስ ታፈሰ ፣ ሳሙኤል ሳሊሶ ፣ ማራኪ ወርቁ እና ኡጉታ ኡዶክን ወደ ኮከብነት የማሸጋገር አላማን ይዘዋል ተብሏል፡፡

PicsArt_1468657355891

1 Comment

  1. it is still to use old players on preimier league. this must be changed seiriosly.

Leave a Reply