የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የ2014 የውድድር ዘመን ድልድል ይፋ ሲሆን መከላከያም ተጋጣሚውን አውቋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስን በመላያ ምቶች አሸንፎ የ2005 የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎማለፍ) ቻምፒዮን የሆነው መከላከያ የ2014 የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመርያ ጨዋታውን ከኬንያው ሊዮፓርድስ ጋር ያደርጋል፡፡ ሰኞ ከቀትር በኋላ በወጣው ድልድል መሰረት መከላከያ የመጀመርያ ጨዋታውን ኬንያ ላይ ሲያደርግ የመልሱን ጨዋታ አአ ላይ ያደርጋል፡፡
መከላከያ ይህንን የቅድመ ማጣርያ ዙር ካለፈ በ1ኛው ዙር የቦትስዋናውን ጋቦሮኒ እና የደቡብ አፍሪካውን ፐርስፖርት ዩናይትድን ያገኛል፡፡
©ሶከር ኢትዮጵያ