የዝውውር መስኮቱ ከተከፈተ ወዲህ በፌዴሬሽኑ የተረጋገጠው የአብዱልከሪም ዝውውር ብቻ ነው

የክረምቱ የዝውውር መስኮት ተከፈተ ዛሬ 9ኛ ቀኑን ቢይዝም የተቀዛቀዘ አጀማመር እያሳየ ይገኛል፡፡ በ9ኙ ቀናት ተጫዋቾች በክለባቸው ውላቸውን ለማደስ እና ወደ አዲስ ክለብ ለማምራት እንዲሁም ለአሰልጣኞች ቅጥር በቃል ደረጃ ከመስማማት ውጪ በፌዴሬሽን ተገኝነተው ውል ማሰር አልቻሉም፡፡

የዝውውር መስኮቱ ከተከፈተበት ሐምሌ 1 ጀምሮ በጠቅላላ የተመዘገቡ ውሎች ቁጥር ሶስት ብቻ ሲሆን እነዚህም አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ለድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝነት የተስማሙበት ፣ አብዱልከሪም ሀሰን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለቆ ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለበት እንዲሁም ኤፍሬም ወንድወሰን በኢትዮጵያ ቡና ውሉን ለ2 አመታት ያደሰባቸው ውሎች ብቻ ናቸው፡፡

PicsArt_1468681978076

በተለምዶ ክለቦች የዝውውር መስኮቱን መጀመር በመጠቀም በፍጥነት በርካታ ተጫዋቾችን በማስፈረም ወደ ዝግጅት የመግባት ልማድ ቢኖራቸውም ዘንድሮ ተጫዋቾችን በገፍ ከማስፈረም ይልቅ የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል በማደስ እና ከተስፋ ቡድኖቻቸው ተጫዋቾችን በማሳደግ ላይ ያተኮሩ ይመስላሉ፡፡

ምናልባትም ክለቦች የተጫዋቾቻቸውን ውል የማደስ እንቅስቃሴያቸው ፍሬ ካላፈራ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደማስፈረም ሊገቡ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም የብሄራዊ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር በቀጣዩ ሳምንት የሚጀመር በመሆኑ እና ከፍተኛ ሊጉ ወደ መገባደዱ በመቃረቡም በቀጣዮቹ ሳምንታት የክለቦች የዝውውር እንቅስቃሴ ሞቅ እያለ እንደሚሄድ ይጠበቃል፡፡

2 Comments

Leave a Reply