ሀ-17 ፕሪሚየር ሊግ፡ የማጠቃለያ ውድድሩ ዛሬ ሲጀመር አዳማ ከተማ ድል ቀንቶታል

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር የኢትዮጵያ እግር኿ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲ ባሻ በተገኙበት ተከፍቷል፡፡ በመክፈቻው በተደረጉት ጨዋታዎችም አዳማ ድል ሲቀናው ደደቢት ከ ንግደ ባንክ ነጥብ ተጋርተዋል፡፡

08:00 ላይ ባለሜዳው አዳማ ከተማ መከላከያን 1-0 በማሸነፍ ውድድሩን በድል ከፍቷል፡፡ እምብዛም ማራኪ እንቅስቃሴ ባልታየበት ጨዋታ በእለቱ ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ኢሳ ንጉሴ የጨዋታው መጠናቀቅያ ፊሽካ ሲጠበቅ ወሳኟን ብቸኛ ጎል አስቆጥሮ አዳማን ለድል አብቅቷል፡፡

PicsArt_1468689118242

በዕለቱ ጨዋታውን የሚመሩት ዋና ዳኛ በጉዳት ምክንያት ጨዋታውን መቀጠል ባለመቻላቸው አራተኛው ዳኛ ቀሪውን ጨዋታ በመምራት አጠናቀዋል፡፡

PicsArt_1468688313987

10:00 ላይ ሲጠበቅ የነበረው የደደቢት እና ንግድ ባንክ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተፈፅሟል፡፡ በወጣቶች እግርኳስ በተገናኙ ቁጥር ከፍተኛ ፉክክር የሚስተናገድበት ይህ ጨዋታ ዛሬም ፍትጊያ እና ሀይል የተቀላቀለበት ጨዋታ አስተናግዷል፡፡

ዳንኤል ጌድዮን ደደቢትን ቀዳሚ ሲያደርግ ገመቺሳ አማኑኤል ንግድ ባንክን አቻ አድርጓል፡፡

PicsArt_1468688250280

በርካታ ቁጥር ያለው የስፖርት ቤተሰብ በተከታተለው ጨዋታ ላይ የስቴዲዮሙ ድባብ ትኩረት ይስብ የነበረ ሲሆን አንድ የውጭ ዜጋ በድጋፍ አሰጣጡ በስቴዲዮሙ የነበሩት ተመልካችን ሲያዝናና ውሏል፡፡

PicsArt_1468688081534

የማጠቃለያ ውድድሩ ነገ ሲቀጥል በምድብ ሀ 08:00 ላይ ሀዋሳ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፤ 10:00 ላይ ሐረር ሲቲ ከ አአ ከተማ ይጫወታሉ፡፡

Leave a Reply