ኮንፌድሬሽን ካፕ፡ ኤምኦ ቤጃያ እና ቲፒ ማዜምቤ ነጥብ ተጋርተዋል

በካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ የምድብ አንድ መሪው ቲፒ ማዜምቤ ከሜዳው ውጪ ከኤምኦ ቤጃያ ጋር ያለግብ አቻ ተለያይቷል፡፡

የሁለት ነጥብ ልዩነት ብቻ የነበራቸው ሁለቱ ክለቦች ባለመሸናነፋቸው የደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ለውጥ ሳይመጣ ቀርቷል፡፡ በንፅፅር ምድብ ውስጥ ካሉት ለቲፒ ማዜምቤ አስቸጋሪ የሆነው ቤጃያ የነበረ ቢሆንም በካፍ ውድድሮች ከፍተኛ ልምድ ያለው አለመሆኑ ለቲፒ ማዜምቤ ነገሮች አቅልሏል፡፡

ጉሽሚያዎች በበዙበት ጨዋታ ቤጃያ የአምስት ግዜ የአፍሪካ ሻምፒዮኖቹን በጨዋታ መብለጥ የቻሉ ቢሆንም ቀላል የግብ ማግባት አጋጣሚዎችን አምክነዋል፡፡ ኢስማኤል ቤልካሲም ቤጃያን መሪ ማድረግ የምትችል ኳስ ሲያመክን ቻዳዊው ኢንተርናሽናል ሞርጋን ቤቶራንጋል ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት ጥሩ የማግባት አጋጣሚን ቢያገኝም ኳሷ ወደ ውጪ ሰድዷታል፡፡

የአቻ ውጤቱን ተከትሎ ማዜምቤ በሰባት ነጥብ የምድቡ አናት ላይ ሲቀመጥ ቤጃያ በአምስት ነጥብ ሁለተኛ ነው፡፡ PicsArt_1468823449931

የዕሁድ ውጤት

ሞሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያ (አልጄሪያ) 0-0 ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)

ቀጣይ ጨዋታዎች

ማክሰኞ ሃምሌ 20/2008

15፡00 – ሚዲአማ (ጋና) ከ ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) (ኢሲፖንግ ስፖርትስ ስታዲየም)

19፡00 – አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) ከ ኤቷል ስፖርቲቭ ደ ሳህል (ቱኒዚያ)

ረቡዕ ሃምሌ 21/2008

15፡30 – ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ከ ሞሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያ (ስታደ ቲፒ ማዜምቤ)

21፡30 – ፋት ዩኒየንስ ስፖርት ራባት (ሞሮኮ) ከ ካውካብ አትሌቲክ ክለብ ማራካሽ (ሞሮኮ) (ኮምፕሌክስ ስፖርቲፍ ሞላይ አል ሃሰን)

Leave a Reply