ቻምፒየንስ ሊግ፡ ሰንዳውንስ ከሜዳው ውጪ ዛማሌክን አሸንፏል

የደቡብ አፍሪካው ሻምፒዮን ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ካይሮ ላይ ዛማሌክን በመርታት ምድብ ሁለትን መምራት ጀምሯል፡፡

በቻምፒየንስ ሊጉ ከሜዳ ውጪ ጠንካራ አቋማቸውን እያሳዩ የመጡት ‘ብራዚሎቹ’ ዛማሌክን 2-1 ማሸነፍ ችለዋል፡፡ ሰንዳወንስ በ19ኛው ደቂቃ በቲያኒ ማቡንዳ አማካኝነት ቀዳሚ መሆን ሲችል ዛማሌኮች ግብ ከተቆጠረባቸው በኃላ በተደጋጋሚ የሰንዳውንስ ተከላካይ መስመር መፈተን ችለዋል፡፡ በ37ኛው ደቂቃ በረጅሙ ወደ ሰንዳውንስ ግብ ክልል የተላከውን ኳስ ተከላካዩ ታቦ ንቴቴ እና የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ጠባቂ ዴኒስ ኦኒያንጎ ስህተት መሃመድ ኢብራሂም ዛማሌክን አቻ አድርጓል፡፡

ከዕረፍት መልስ በተደጋጋሚ የማጥቃቱን የበላይነት የወሰዱት ዛማሌኮች ቢሆኑም በ66ኛው ደቂቃ የዚምባቡዌው ኢንተርናሽናል ካማ ቢልአት የሰንዳውንስን የማሸነፊያ ግብ የአህመድ ኤል ሸናዊ መረብ ላይ አሳርፏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ በፒትሶ ሞሴሚኒ የሚለጥነው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ምድቡን በስድስት ነጥብ ሲመራ ዛማሌክ በሶስት ተከታዮን ደረጃ ይዟል፡፡ ኢኒምባ የምድቡን ግርጌ ያለምንም ነጥብ ይዟል፡፡

PicsArt_1468825501775

የዕሁድ ውጤት

ዛማሌክ (ግብፅ) 1-2 ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ)

ቀጣይ ጨዋታዎች

ረቡዕ ሃምሌ 21/2008

15፡30 – አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቯር) ከ ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) (ስታደ ሮበርት ቻምፕሮ)

19፡30 – ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ) ከ ዛማሌክ (ግብፅ) (ሉካስ ማስተርፒስስ ሞርፒ ስታዲየም)

19፡30 – ዋይዳድ አትሌቲክ ክለብ (ሞሮኮ) ከ አል አሃሊ (ግብፅ) (ኮምፕሌክስ ፕሪንስ ሞላይ አብደላ ስታዲየም)

 

Leave a Reply