አስቻለው ግርማ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሲመለስ ኤልያስ ውሉን ማደሱን ኢትዮጵያ ቡና አስታውቋል

ኢትዮጵያ ቡና የውል ዘመነን ያጠናቀቀው ኤልያሰስ ማሞን ማስፈረሙን እንዲሁም ባለፈው ክረምት ክለቡን ለቆ የነበረው አስቻለው ግርማን ማስፈረሙን በይፋዊ የክለቡ ፌስቡክ ገፅ አስታውቋል፡፡


ክለቡ በፌስቡክ ያሰፈረው መረጃ ይህንን ይመስላል፡-

” ኤልያስ ማሞ ከክለባችን ይለቃል የሚሉ ወሬዎች ሲናፈሱ ቢቆዩም እርሱ ግን ተወዳጁን ክለቤን አልለቅም በማለት ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ከክለባችን ጋር የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል፡፡

አስቻለው ግርማም በተመሳሳይ ለሁለት ዓመት የሚያቆየውን ፊርማ በዛሬው እለት አስቀምጧል፡፡”


በ2005 ሱሉልታ ከተማን ለቆ ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለው አስቻለው ባለፈው ክረምት በአንድ አመት ውል ሀዋሳ ከተማን የተቀላቀለ ሲሆን ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል፡፡
ስሙ ከደደቢት እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ተያይዞ የቆየው ኤልያስ ማሞ በመጨረሻም ውሉን አራዝሟል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *