ሙጂብ ቃሲም ለአዳማ ለመፈረም ሲስማማ ሌሎች 5 ተጫዋቾችም ክለቡን ለመቀላቀል ተስማምተዋል

አዳማ ከተማ ዘንድሮም የዝውውር መስኮቱ ዋንኛ ተዋናይ መሆኑን ከወዲሁ እያሳየ ይገኛል፡፡ በርካታ ተጫዋችችን ለማስፈረም የተሰማማ ሲሆን በውድድር ዘመኑ እምብዛም ያልተጠቀመባቸው ተጫዋቾችን እንደሚለቅ ከክለቡ አካባቢ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አዳማ የቀድሞው ከ20 አመት ብሄራዊ ቡድን አጥቂ ኤፍሬም ቀሬን ከሙገር ሲሚንቶ  ፣ በቡና የተለቀቀው ጥላሁን ወልዴ ፣ የደደቢቱን የተከላካይ አማካይ ኄኖክ ካሳሁን እንዲሁም ከባንክ የለቀቀው ሲሳይ ቶሊ እና ስሙ ያልተጠቀሰ ተጫዋች ከከፍተኛ ሊግ ክለብ ለአዳማ ለመፈረም የተስማሙ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ ሙጂብ ቃሲም ሀዋሳን ለቆ አዳማ ከተማ ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል፡፡

ሙጂብ ቃሲም ከሀዋሳ የኮንትራት ማደሻ ጥያቄ ቢቀርብለትም በሲዳማ ካሰለጠኑት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጋር በድጋሚ መገናኘትን ቅድሚያ ሰጥቷል፡፡

ሙጂብ አዳማን መቀላቀሉን ተከትሎ በሲዳማ ቡና የተከላካይ ክፍል አጋሩ ከነበረው ሞገስ ጋር የተከላካይ ክፍሉን ይመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ክለቡን እንደሚለቁ ከሚጠበቁ ተጫዋቾች መካከል በጉዳት መልካም አመት ያላሳለፈው ወንድወሰን ሚልኪያስ ስሙ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ሲያያዝ ተከላካዩ ምንተስኖት ከበደ ወደ መከላከያ ማምራቱ ተሰምቷል፡፡ በአሰልጣኝ አሸናፊ ብዙም የመጫወት እድል ያልተሰጠው ቢንያም አየለ ወደ ትውልድ ከተማው ድሬዳዋ ተመልሶ ለድሬዳዋ ከተማ እንደሚፈርም የሚጠበቅ ሲሆን በዲሲፕሊን ምክንያት በክለቡ የተቀጣው ወድሜነህ ዘሪሁን ፣ ሲሳይ ባንጫ ፣ ጫላ ድሪባ እና ዮናታን ከበደ ክለቡን እንደሚለቁ የሚጠበቁ ሌሎች ተጫዋቾች ናቸው፡፡ ዮናታን ክለቡን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ከሀዋሳ ከተማ እና ሁለት የአአ ክለቦች ጋር ድርድር እያደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡

PicsArt_1468847522279

ጥላሁን IN ፤ ዮናታን OUT

የደሳለኝ ደባሽ እና ሚካኤል ጆርጅን ውል ለማደስ ከስምምነት የደረሱት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ተጨማሪ ተከላካይ ለማስፈረም እየተንቀሳቀሱ ሲሆን ፍለጋቸውን ከፕሪሚየር ሊጉ በተጨማሪ በከፍተኛ ሊግ ላይም አድርገዋል፡፡

2 Comments

Leave a Reply