አዲሱ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው በይፋ ከተሾሙ ወዲህ በተጫዋች ግዢ ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
አሰልጣኙ የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎችን ተዟዙረው የተመለከቱ ሲሆን ትኩረታቸውን የሳቧቸው 4 ተጫዋቾችን የግላቸው አድርገዋል፡፡ በቀጣዮቹ ቀናትም የተጫዋቾቹ ማንነት ይታወቃሉ ተብሏል፡፡
ድሬዳዋ የዳሽኑን ግብ ጠባቂ ቢንያም ሀብታሙ ወደ ትውልድ ከተማው ሲመልስ ከአሰልጣኙ ጋር በሲዳማ ቡና አብረው የሰሩት አሳምነው አንጀሎ እና ዘነበ ከበደ ለክለቡ ለመፈረም ተስማምተዋል፡፡ ከአዳማ ከተማ የተለቀቀው ቢንያም አየለም ወደ ድሬዳዋ ከተማ የሚመልሰውን ዝውውር ለማድረግ ተቃርቧል፡፡
ብርቱካናማዎቹ ካስፈረሟቸው ተጫዋቾች ባሻገር ውሉን የጨረሰው ዳዊት እስጢፋኖስን ኮንትራት ለማደስ በድርድር ላይ የሚገኝ ሲሆን በአጭር ጊዜ ኮንትራት ድሬዳዋን የተቀላቀለው ዮርዳኖስ አባይ በቀጣዩ አመትም ከክለቡ ጋር ለመቆየት በመደራደር ላይ ይገኛል፡፡
አሁን ባገኘነው መረጃ ደግሞ ዳዊት እስጢፋኖስ ከክለቡ ጋር የመቀጠሉ ነገር ያበቃለት እንደሆነ ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡