ዳዊት እስጢፋኖስ እና ዮርዳኖስ አባይ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር አይቀጥሉም

በአጭር ጊዜ ውሎች ወደ ድሬዳዋ ከተማ ያቀኑት ዳዊት እስጢፋኖስ እና ዮርዳኖስ አባይ ከክለቡ እንደሚለቁ ከክለቡ አካባቢ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የነበረውን ውዝግብ በህዳር ወር ፈትቶ እስከ አመቱ መጨረሻ በሚዘልቅ ኮንትራት ወደ ድሬዳዋ ከተማ ያቀናው ዳዊት እስጢፋኖስ ከክለቡ ጋር ለተጨማሪ አመታት የሚያቆየው ውል ሳይቀርብለት በመቅረቱ ከክለቡ እንደሚለቅ ታውቋል፡፡

PicsArt_1468955326350

ከድሬዳዋ ፖሊስ በ6 ወር ኮንትራት ወደ ድሬዳዋ ያመራው ዮርዳኖስ አባይም በተመሳሳይ በክለቡ ባለመፈለጉ ክለቡን እንደሚለቅ ከምንጮቻችን ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ዳዊት ወደ ቀድሞ ክለቡ ኢትዮጵያ ቡና ሊመለስ እንደሚችል እየተነገረ ሲሆን የዮርዳኖስ አባይ የወደፊት እጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን አልታወቀም፡፡

Leave a Reply