ስለ ፋሲል ከተማ ስኬት ተጫዋቾቹ ይናገራሉ. . .

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2008 የውድድር ዘመን ፋሲል ከተማ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደጉን ያረጋገጠ ቀዳሚው ክለብ ሆኗል፡፡

ለፋሲል የውድድር አመቱ ስኬት ከሚጠቀሱት ቁልፍ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው አብዱልራህማን ሙባረክ እና አምበሉ ታደለ ስለ ክለባቸው ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደግ የሰጡትን አስተያየት እንዲህ አቅርበነዋል፡፡

“ከነበረን ህብረትና ፍቅር የተነሳ ወደ ሊጉ ባናድግ ነበር የሚገርመኝ” አብዱልራህማን ሙባረክ

ስለ ውድድር አመቱ

” ከፍተኛ ሊጉ በአዲስ ፎርማት መካሄድ የጀመረ የመጀመርያው ውድድር በመሆኑ ሁሉም ክለቦች ፕሪሚየር ሊግ ለመግባት ካላቸው ፍላጎት የተነሳ እያንዳንዱ ጨዋታ  በጣም ከባድ ነበር፡፡”

የስኬት ምስጢር

” እውነት ነው የምነግርህ ሁሉም ቡድን ውስጥ ችግር ይኖራል፡፡ ነገር ግን በፋሲል ከተማ እኔ እስከማውቀው ድረስ በአሰልጣኙ ፣ ቡድን መሪው እና ተጨዋቾቹ መካከል የነበረው ግንኙነት ደስ ይል ነበር፡፡ እርስ በእርሳችን ተነጋግረን የምንፈታቸው ነገሮች የሚያስደስት ነበር፡፡ ከነበረን ህብረትና ፍቅር የተነሳ ወደ ሊጉ ባናድግ ነበር የሚገርመኝ፡፡ ፍቅራችን ለዚህ አብቅቶናል፡፡”

በግሉ ስላሳለፈው ጥሩ አመት

እኔ እንግዲህ አምና ከነበረኝ እንቅስቃሴ አንጻር ብዙ ጎል ባላስቆጥርም ዘንድሮ  ለነበረኝ መልካም እንቅስቃሴ አሰልጣኙ የሚሰጠኝ ነፃነት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ለኔ ብቻ ሳይሆን ለእያንዳንዱ ተጨዋች የሚሰጠው ነፃነት ያለ ጫና እንድንጫወት ማድረጉ ራሳችንን እንድናገኘው ያደርገናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከበስተጀርባዬ የኔ የምላቸው ሰዎች የሚያደርጉልኝ ድጋፍ ለዚህ አብቅቶኛል፡፡

PicsArt_1469120810080

” ከስኬታችን ጀርባ የደጋፊያችን አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር”  ታደለ ባይሳ

ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደጋቸው የፈጠረበት ስሜት

” ስሜቱ በጣም ከባድ ነው፡፡ በፋሲል ቤት አምስት አመት ቆይቻለው ፤ ለኔ የዛሬዋ ቀን የተለየች ናት፡፡

የስኬት ምስጢር

” ውድድሩ እጅግ በጣም አድካሚና ፈታኝ ነው፡፡ የውጤት መሰረቱ የቡድን ህብረታችን ፣ ፍቅራችን እና አንድነታችን ነው፡፡ በነበሩብን ድክመቶች ሁሉ  እየተነጋገርን አሰልጣኛችን የሚሰጠንን ተቀብለን ከፈጣሪ እርዳታ ጋር እዚህ ደርሰናል፡፡”

የደጋፊ አስተዋጽኦ

“ከስኬታችን ጀርባ በየሄድንበት ሀገር አብረውን በመጓዝ ከጎናችን ሆነው ያበረታቱን የነበሩት ደጋፊቻችን አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለደጋፊዎቻችን እንኳን ደስ አላቹ ማለት እፈልጋለው፡፡ “

1 Comment

  1. Dear readers when you read my comment please use fan instead of fun.Thank you for your understanding.

Leave a Reply