U17 ፕሪሚየር ሊግ ፡ በ6ኛ ቀን የማጠቃለያ ውድድር ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና አሸንፈዋል

ስድስተኛ ቀኑን የያዘው የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ የማጠቃልያ ውድድር ተጋግሎ ሲቀጥል ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና ድል ቀንቷቸዋል፡፡

08:00 ላይ በተካሄደው የእለቱ የመጀመርያ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐረር ሲቲን 2-1 በማሸነፍ የመጀመርያ ድሉን አስመዝግቧል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለቱንም የድል ጎሎች እንደልቡ ደሴ ሲያስቆጥር የሐረር ሲቲን ብቸኛ ጎል ታዲዮስ አዱኛ አስቆጥሯል፡፡

PicsArt_1469123706761

10:00 ላይ በተካሄደውና ከፍተኛ ፉክክር ከበርካታ ካርዶች በታየበት ጨዋታ ሲዳማ ቡና ሀዋሳ ከተማን በመጨረሻው ደቂቃ በተቆጠረ ጎል 3-2 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜው የመግባት እድሉን አስፍቶ ወጥቷል፡፡

የሲዳማ ቡናን የድል ጎሎች ይገዙ ቦጋለ (2) እና አዲሱ ተስፋዬ ሲያስቆጥሩ የሀዋሳን ጎል ምንተስኖት ማቲያስ እና ወንድማገኝ ታደሰ አስቆጥረዋል፡፡

PicsArt_1469124157995

ውድድሩ ነገም ሲቀጥል ከምድብ ለ 08:00 ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ወላይታ ድቻ ፤ 10:00 ላይ መከላከያ ከ ደደቢት ይጫወታሉ፡፡

 

ኮከብ ጎል አስቆጣሪዎች

3 የኋላሸት (አዳማ ከተማ)

3 እንደልቡ ደሴ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

1 Comment

Leave a Reply