ዮሃንስ በዛብህ ለኢትዮጵያ ቡና ፈርሟል

ኢትዮጵያ ቡና የሀዋሳ ከተማው ግብ ጠባቂ ዮሃንስ በዛብህን ማስፈረሙን በይፋ አስታውቋል፡፡

ዮሃንስ በዛብህ በ2006 ክረምት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለቆ ሀዋሳ ከተማን የተቀላቀለ ሲሆን በመጀመርያው አመት የቡድኑ ቋሚ ተሰላፊ መሆን ችሎ ነበር፡፡ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ግን የደብብ  አፍሪካዊው ብሪያን ቴቤጎ መምጣት ተከትሎ ተጠባባቂ ለመሆን ተገዷል፡፡

ዮሃንስ ከሀዋሳ ጋር ለተጨማሪ አመታት የሚያቆየውን ውል ለማደስ ድርድር ላይ የነበረ ቢሆንም በመጨረሻም ለኢትዮጵያ ቡና የ2 አመት ኮንትራት ፈርሟል፡፡

የዮሃንስ ለቡና መፈረም ከሀሪሰን ሄሱ እና ወንድወሰን በተጨማሪ ለክለቡ የግብ ጠባቂ አማራጭ ይፈጥርለታል፡፡

Leave a Reply