የኢትዮጵያ ከ17 አመት ፕሪሚየር ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ቀጥለዋል፡፡ ዛሬ 7ኛ ቀኑን በያዘው ውድድር መከላከያ ድል ሲቀናው ንግድ ባንክ ከ ወላይታ ድቻ አቻ ተለያይተዋል፡፡
08:00 ላይ በተደረገው ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ወላይታ ድቻ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች የማለፍ ተስፋቸውን ለማለምለም ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ ቢጠበቅባቸውም ሳይሸናነፉ ጨዋታቸውን ፈጽመዋል፡፡
10:00 ላይ መከላከያ ደደቢትን 2-1 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የማለፍ ተስፋውን አለምልሟል፡፡
የመከላከያን ሁለቱንም የድል ግቦች ዮሐንስ ደረጄ ከመረብ ሲያሳርፍ የደደቢትን ጎል በዛብህ ኩምሳ አስቆጥሯል፡፡
ዮሃንስ ዛሬ ያስቆጠራቸውን ግቦች ጨምሮ የግብ መጠኑን 4 በማድረስ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን በመምራት ላይ ይገኛል፡፡
የነገጨዋታዎች
08:00 አአ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ
10:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሲዳማ ቡና
ኮከብ ጎል አስቆጣሪዎች
4 ዮሃንስ ደረጄ (መከላከያ)
3 የኋላሸት ፍቃዱ (አዳማ ከተማ)
3 እንደልቡ ደሴ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)