ሁለቱ ጦሮች እሁድ ይጫወታሉ

በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ደደቢት እና መከላከያ የመልስ ጨዋታቸውን በመጪው እሁድ ያደርጋሉ፡፡

ባለፈው እሁድ ከከፍተኛ የጨዋታ ብልጫ ጋር የዛንዚባሩን ኬኤምኤኤም 3-0 የረታው ደደቢት የመልስ ጨዋውን ለማድረግ ረቡእ ወደ ስፍራው አቅንቷል፡፡ ሰማያዊው ጦር ጨዋታውን እዚህ ጨርሶት እንደመሄዱ እና ከዛንዚባሩ ሻምፒዮን ደካማነት አንፃር ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድሉ ከሞላ ጎደል የተረጋገጠ ይመስላል፡፡

ከደደቢት በኩል የመስመር ተከላካዩ ስዩም ተስፋዬ እና ግብ ጠባቂው ታሪክ ጌትነት በጉዳት ጨዋታው ያመልጣቸዋል ተብሏል፡፡

በመጀመርያ የአፍሪካ ውድድር ጨዋታቸው ድል ያስመዘገቡት የደደቢቱ አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ በተከላካይ መስመራቸውን እና የአጥቂዎቻቸውን ግብ የማስቆጠር ድክመት ለማሻሻል እንደሚጥሩ ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ አሁድ ወደ ናይሮቢ አቅንቶ በኤኤፍሲ ሊዮፓርድስ 2-0 የተረታው መከላከያ የመልስ ጨዋታውን እሁድ 10 ሰአት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያደርጋል፡፡

ጦሩ ግብ ሳያስቆጥር በመመለሱ ጨዋው እጅጉን ሊከብደው እንደሚችል ቢነገርም አሰልጣኝ ገብረመድን ግን ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የሚችሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

ከመከላከያ በኩል ተከላካዩ ገብረወልድ በጉዳት ጨዋታው የሚያመልጠው ሲሆን ሲሳይ ደምሴ ከቅጣት መልስ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *