የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ሲጠናቀቁ ሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል፡፡
10:00 ላይ በወንጂ ሜዳ ጨዋታቸውን ያደረጉት ሐረር ሲቲ እና ሲዳማ ቡና 1-1 አቻ ተለያይተዋል፡፡ ብሩክ ሰሙ ለሐረር ሲቲ ሲያስቆጥር አንለይ የሲዳማ ቡናን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና ነጥቡን 8 በማድረስ የደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ በመቀመጥ ወደ ግማሸ ፍጻሜው ተቀላቅሏል፡፡
በተመሳሳይ 10:00 አዳማ አበበ ቢቂላ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አበባ ከተማን ወንድወሰን ቢራራ ባስቆጠረው ግብ 1-0 ቢያሸንፍም ወደ ግማሽ ፍጻሜው ለማለፍ በቂ አልሆነለትም፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀዋሳ ከተማ ጋር እኩል 7 ነጥብ ቢይዝም በግብ ልዩነት ተበልጦ ከምድቡ ተሰናብቷል፡፡
የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች በመጪው ሀሙስ አዳማ አበበ ቢቂላ ላይ ሲደረጉ 07:00 ላይ ሲዳማ ቡና ከ መከላከያ ፤ 09:00 ላይ አዳማ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ ይጫወታሉ፡፡
ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች
4 ዮሐንስ ደረጄ (መከላከያ)
3 የኋላሸት ፍቃዱ ( አዳማ ከተማ)
3 እንደልቡ ደሴ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
2 ታዲዮስ አዱኛ (ሐረር ሲቲ)
2 ወንድማገኝ ታደሰ (ሀዋሳ ከተማ)
2 ምንተስኖት ማቲዮስ (ሀዋሳ ከተማ)
2 ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና)
2 ኢሳ ንጉሴ (አዳማ ከተማ)
2 ዳንኤል ጌድዮን (ደደቢት)