ብሄራዊ ሊግ ፡ በማጠቃለያ ውድድሩ 3ኛ ቀን ውሎ ሶሎዳ አድዋ ፣ ከፋ ቡና እና ለገጣፎ ድል ቀንቷቸዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ የማጠቃልያ ውድድር በባቱ (ዝዋይ) ከተማ መከናወኑን ቀጥሏል፡፡ 3ኛ ቀኑን በያዘው ውድድርም ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ከፋ ቡና ፣ ሶሎዳ አደዋ እና ለገጣፎ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

08:00 ላይ በባቱ ሜዳ ከፋ ቡና ከ ወሊሶ ከተማ ባደረጉት የምድብ ሐ ጨዋታ ከፋ 2-1 አሸንፏል፡፡

የከፋ ቡናን የድል ጎሎች ምንተስኖት ታረቀኝ እና ተካልኝ መስፍን ሲያስቆጥሩ የወሊሶን ብቸኛ ጎል ሙሴ እንዳለ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ 08:00 በሼር ሜዳ በተካሄደው የምድብ መ ጨዋታ ሶሎዳ አደዋ ሽሬ እንደስላሴን 2-1 አሸንፏል፡፡ የሶሎዳ አደዋን የድል ጎሎች ሽብሪል ጅራታ እና በፍቃዱ አለማየሁ ሲያስቆጥሩ የሽሬ እንደስላሴን ብቸኛ ጎል ያሲን አህምድ አስቆጥሯል፡፡

PicsArt_1469466114102

10:00 ላይ በባቱ ሜዳ ከምድብ ሐ በተደረገ ሌላ ጨዋታ ዞናቸውን በቻምፒዮንነት ያጠናቀቁት መተሀራ ስኳር እና አንበሪቾ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ወንድወሰን ምህረቴ አንበሪቾን ቀዳሚ ሲያደርግ ዮርዳኖስ ዮሃንስ መተሃራ ስኳርን አቻ ያደረገች ግብ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ 10:00 በሼር ሜዳ ላይ ከምድብ መ በተደረገ ጨዋታ ለገጣፎ ከተማ ዳባት ከተማን 2-1 አሸንፏል፡፡ የለገጣፎን የድል ጎሎች ብሩክ መርጊያ እና ልደቱ ለማ ሲያስቆጥሩ የዳባት ከተማን ብቸኛ ጎል ግዮን መላኩ አስቆጥሯል፡፡

ውድድሩ ነገ በእረፍት ምክንያት የማይደረግ ሲሆን ረቡዕ 2ኛ የምድብ ጨዋታዎች ይጀምራሉ፡፡

ረቡዕ 20/11/2008

04:00 ደሴ ከ አማራ ፖሊስ (ሼር ሜዳ)

04:00 ሚዛን አማን ከ አራዳ ክ/ ከተማ (ባቱ ሜዳ)

10:00 ወልቂጤ ከተማ ከ ሞጆ ከተማ (ሼር ሜዳ)

10:00 ዲላ ከተማ ከ ቡታጅራ ከተማ (ባቱ ሜዳ)

7 Comments

  1. እናመሰግናለን ሶከር ኢትዮጵያ፤ በተረፈ ‘አደዋ’ የሚለው ወደ ‘ዓድዋ’ ይስተካከል!

  2. ከፋ ሳይሆን…….ካፋ በሚል ይስተካከል

  3. የለገጣፎን ግብ ያሥቆጠረው ብሩክ በርጌ ሣይሆን ብሩክ መርጊያ በሚል ይሥተካከል

Leave a Reply