ኢትዮጵያ ቡና አዲስ የቴክኒክ ዳይሬክተር ሾመ

ኢትዮጵያ ቡና አቶ ደምሰው ፍቃዱን አዲሱ የክለቡ የቴክኒክ ዳይሬክተር አድርጎ ሾሟል፡፡

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን አጋማሽ ደሳለኝ ግርማን ከቴክኒክ ዳይሬክተርነት ያሰናበተው ኢትዮጵያ ቡና በቦታው ላይ ቅጥር ሳይፈፅም የቆየ ሲሆን ከቀናት በፊት አቶ ደምሰውን መሾሙ ታውቋል፡፡

አቶ ደምሰው በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በተለያዩ ክለቦች ተጫውተው አሳልፈዋል፡፡

አዲሱ የቴክኒክ ዳይሬክተር በአሁኑ ሰአት በዝዋይ ከተማ የሚገኙ ሲሆን በስፍራው እየተደረገ ከሚገኘው የብሄራዊ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር ተጫዋቾችን በመመልመል ላይ ይገኛሉ፡፡ የቡና ረዳት አሰልጣኝ ገዛከኝ ከተማ ፣ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ውብሸት ደሳለኝ እና ቡድን መሪው አቶ ሰይፈ ዘርጋባቸውም በዝዋይ ይገኛሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *