ለዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት 28 ተጫዋቾች ተጠርተዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ዋልያዎቹ በነሀሴ ወር መጨረሻ ከሲሸልስ ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ ጨዋታ 28 ተጫዋቾችን መርጠዋል፡፡

በዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት መካከል ተክለማርያም ሻንቆ ፣ መሃሪ መና እና አዲስ ግደይ ለመጀመርያ ጊዜ ጥሪ ሲደርሳቸው ዋሊድ አታ ፣ ቴዎድሮስ በቀለ ፣ ተስፋዬ አለባቸው እና እንዳለ ከበደ ወደ ቡድኑ የሚመልሳቸው ጥሪ ደርሷቸዋል፡፡

በአንጻሩ የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋች አስቻለው ታመነ ፌደዴሬሽኑ ይፋ ካደረገው ዝርዝር የተዘለለ ተጫዋቾች ነው፡፡ አስቻለው በሁለት ቢጫ ቅጣት ምክንያት ከሲሸልስ ጋር የሚደረገው ጨዋታ የሚያመልጠው በመሆኑ ጥሪው ሳይደርሰው ቀርቷል፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ከሐምሌ 25 ቀን 2008 ጀምሮ ጨዋታ በሚያደርግበት ሀዋሳ ዝግጅቱን እንደሚያካሂድ ታውቋል፡፡

 ግብ ጠባቂዎች 

ጀማል ጣሰው (መከላከያ) ፣ ሳምሶን አሰፋ (ድሬዳዋ ከተማ) ፣ አቤል ማሞ (ሙገር ሲሚንቶ) ፣ ተክለማርያም ሻንቆ (አአ ከተማ)

 ተከላካዮች 

አዲስ ተስፋዬ (መከላከያ) ፣ ቴዎድሮስ በቀለ (መከላከያ) ፣ መሐሪ መና (ቅዱስ ጊዮርጊስ)  ፣ አብዱልከሪም መሃመድ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ አህመድ ረሽድ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ሙጂብ ቃሲም (አዳማ ከተማ) ፣ ስዩም ተስፋዬ (ደደቢት) ፣ አንተነህ ተስፋዬ (ሲዳማ ቡና) ፣ ዋሊድ አታ (ኦስተርሰንድ / ስዊድን)

 አማካዮች

ተስፋዬ አለባቸው (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ በሃይሉ አስፋ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ጋቶች ፓኖም (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ኤልያስ ማሞ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ሽመክት ጉግሳ (ደደቢት) ታደለ መንገሻ (አርባምንጭ ከተማ) ፣ እንዳለ ከበደ (አርባምንጭ ከተማ) ፣ ኤፍሬም አሻሞ (ደደቢት) ፣ አስራት መገርሳ (ዳሽን ቢራ) ፣ አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና) ፣ ሽመልስ በቀለ (ፔትሮጄት /ግብጽ)

 አጥቂዎች 

ሳላዲን ሰይድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ታፈሰ ተስፋዬ (አዳማ ከተማ) ፣ ዳዊት ፍቃዱ (ደደቢት) ፣ ጌታነህ ከበደ (ቢድቬትስ ዊትስ/ደቡብ አፍሪካ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *