የቅዱስ ጊዮርጊሱ የመስመር አማካይ ምንያህል ተሾመ ባለፈው ሳምንት በሊግ ስፖርት ጋዜጣ ላይ በሰጠው አስተያየት ምክንያት ውዝግብ መፍጠሩን ተከትሎ ዛሬ ይቅርታ ጠይቋል፡፡ ምንያህል ዛሬ ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ እንደተናገረው በስሜታዊነት ተነሳስቶ የተሳሳተ ንግግር እንዳደረገ አምኗል፡፡
‹‹ ከማንም ሰው ጋር የተነካካ ነገር የለኝም ፤ በስሜት ውስጥ ሆኜ ግን ያልተገባ ነገር ተናግሬያለው፡፡ የስፖርት ጋዜጠኞችን በተመለከተ ጋዜጣው ላይ የሰጠሁት አስተያየት ከስሜታዊነት የመነጨ በመሆኑ መላው የስፖርት ጋዜጠኞችን ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡››
ምንያህል የሰጠውን አስተያየት ተከትሎ በበርካታ ሚድያዎች ላይ ይህን አስተያየት እንዳልሰጠ አስተባብሏል ቢባልም አማካዩ ስለ አስተያየቱ ትክክለኛነት ማረጋገጨ ሰጥቷል፡፡
‹‹ በርካታ የሚድያ ሰዎች ደውለውልኛል፡፡ነገር ግን ማንንም አላነጋገርኩም፡፡ ረቡእ እለት ከሊግ ጋር ቃለምልልስ ካደረግኩ በኃላ ለየትኛውም ሚድያ ቃል አልሰጠሁም፡፡›› ሲል አስተባብሏል፡፡ ››