ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በሀዋሳ ዝግጅቱን ቀጥሏል

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከግብፅ ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ከ17 አመት በታች ዋንጫ ማጣርያ የሚያደርገውን ዝግጅት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ከሐምሌ 1 ጀምሮ በሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል በመክተም ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው ብሄራዊ ቡድኑ በመለማመጃ ሜዳ እጦት እንደተቸገረ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በከተማው በርካታ ሜዳዎች ቢገኙም የሚመለከተው አካል ትኩረት በመንፈጉ ለዝግጅት መሰናክል ፈጥሮባቸዋል ተብሏል፡፡

የፌዴሬሽኑ አመራሮች በጉዳዩ ላይ ከቡድኑ ጋር ከተወያዩ በኋላ ችግሩን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚነጋገሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

26 ተጫዋቾች በመያዝ ወደ ሀዋሳ ያቀኑት አሰልጣኝ አጥናፉ ስብስባቸውን ወደ 20 ቀንሰዋል፡፡

PicsArt_1469553202396

በዝግጅት ላይ የሚገኘው ስብስብ ይህን ይመስላል:-

ኦኛ ኦሜኛ ፣ እሸቱ ተሾመ ፣ ፋሲል ገብረሚካኤል ፣ ረመዳን የሱፍ መሃመድ ፣ እሱባለው ጌታቸው ፣ ማትያስ ወልደአረጋዊ ፣ ሚኪያስ መኮንን ፣ አቡበከር ናስር ፣ ዳዊት ሳህሌ ፣ ጫላ ተሸታ ፣ እዮብ አለማየሁ ፣ ዳግማዊ አርአያ አምበፍርድ ፣ ሳሙኤል ተስፋዬ ፣ አማኑኤል አዲሱ ፣ ሉክ ፖውልን ፣ ሀቢብ ከተማ ፣ አላዛር ሽመልስ ፣ ጌታሰጠኝ ሸዋ ፣ አክሊሉ ለአሙ ፣ ቃልኪዳን ዘላለም

PicsArt_1469553254709

3 Comments

  1. Yemaymesil neger b/c Hawassa lay huletun tililik medawoch enkuwan titen binqotir lelmmd aydelem lechawata yedimetinu 6(sidest) medawoch alu silezi lemn yiwashal? …………………..

  2. mikinyat tejemere ######1 keni jima kenema kedebube polise gari lalebet chawota limimid sisera be ikule seat metew zebegnaw silekelekelachew new @ke mikiniyat sira [email protected]

Leave a Reply