የኢትዮዽያ ብሔራዊ ሊግ የማጠቃልያ ውድድር ከአንድ ቀን እረፍት በኋላ በ2ኛ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ሲቀጥል አማራ ፖሊስ እና አራዳ ክ/ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል፡፡
04:00 በባቱ ሜዳ በተካሄደው የምድብ ለ ጨዋታ አራዳ ክ/ከተማ ሚዛን አማንን 2-1 በማሸነፍ ከወዲሁ ወደ ሩብ ፍጻሜው ማለፉን አረጋግጧል፡፡
የአራዳን የድል ጎሎች አማኑኤል አዳነ እና ዮናስ ባቤና ሲያስቆጥሩ የሚዛን አማንን ጎል ናይሮቢ ቦረና አስቆጥሯል፡፡
ሁለቱንም የምድብ ጨዋታዎች የተሸነፈው ሚዛን አማን ከወዲሁ ተሰናባች መሆኑን አረጋግጧል፡፡
በተመሳሳይ 04:00 ላይ በሼር ሜዳ ላይ አማራ ፖሊስ ደሴ ከተማን 4-2 አሸነፏል፡፡
እጅግ ማራኪና ጨዋታና ጠንካራ ፉክክር በታየበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ አማራ ፖሊስ ሁለቴ ከመመራት ተነስቶ አሸንፎ ወጥቷል፡፡
የአማራ ፖሊስ የድል ጎሎችን ሰለሞን መሀመድ ፣ ቴድሮስ አበራ እንዲሁም መሃመድ የሱፍ ተቀይሮ በመግባት ለቡድኑ ወሳኝ ሁለት ጎሎች አስቆጥሯል፡፡ የደሴ ከተማን 2 ግቦች የቀድሞው የወላይታ ድቻ አጥቂ ሳምሶን ቆሊቻ አስቆጥሯል፡፡