ብሄራዊ ሊግ ፡ በማጠቃለያው የከሰአት ውሎ ወልቂጤ እና ቡታጅራ ድል ቀንቷቸዋል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ከአንድ ቀን እረፍት በኋላ በ2ኛ የመድብ ጨዋታዎች ተመልሷል፡፡ ረፋድ 2 ጨዋታ ያስተናገደው ውድድር 10:00 ላይም ቀጥሎ ቡታጅራ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

ባቱ ሜዳ ላይ በተካሄደው የምድብ ለ ጨዋታ ቡታጅራ ከተማ ዲላ ከተማን 1-0 በማሸነፍ የመጀመርያ ድሉን አሳክቷል፡፡  የቡታጅራ ከተማን ብቸኛ የድል ጎል በመጀመርያው አጋማሽ ሳሙኤል ገብሬ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱ ቡታጅራን ለመደገፍ የመጡት በርካታ ደጋፊዎችን አስደስቷል፡፡

PicsArt_1469636525200
PicsArt_1469636993985

በተመሳሳይ 10:00 ላይ ከምድብ ሀ በሼር ሜዳ በተካሄደውና ማራኪ እንቅስቃሴ ከጥሩ የኳስ ፍሰት ጋር በታየበት ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ሞጆ ከተማን 4-1 በሆነ ሰፊ ጎል አሸንፏል፡፡

የወልቂጤን የድል ጎል ጌታነህ ሙሉነህ (2) ፣ ሚካኤል ጋሪ እና ታሪኩ ታምራት ሲያስቆጥሩ የሞጆ ከተማን ብቸኛ ጎል ታመነ ቅባቱ አስቆጥሯል፡፡

PicsArt_1469637046284

ከጨዋታ በፊትና ፍፃሜው ላይ የኢትዮዽያ ህዝብ መዝሙር በመዘመር ለየት ያለ ድጋፍ የሚያሳዮት የወልቂጤ ከተማ ደጋፊዎች ባቱ ከተማን በበጭፈራ ሲያደምቋት አምሽተዋል፡፡

PicsArt_1469636603949

ረፋድ 04:00 ላይ በተደረጉት ጨዋታዎች አማራ ፖሊስ ደሴ ከተማን 4-2 ሲያሸንፍ አራዳ ክ/ከተማ ሚዛን አማንን 2-1 አሸንፏል፡፡

ውድድሩ ነገ ሲቀጥል በምድብ መ ባቱ ሜዳ ላይ በ08:00 ሽረ እንደስላሴ ከ ከለገጣፎ ከተማ ፤ 10:00 ላይ ሶሎዳ አድዋ ከ ዳባት ከተማ ይጫወታሉ፡፡ የምድብ ሐ ጨዋታዎች በሼር ሜዳ ሲደረጉ 08:00 ላይ መተሀራ ስኳር ከ ወሊሶ ከተማ ፤ አምበሪቾ ከ ካፋ ቡና የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *