የኢትዮዽያ ብሄራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር የምድብ ሐ አና መ 2ኛ ጨዋታዎች ዛሬ ተከናውነው መተሃራ ፣ ዳባት እና ካፋ ቡና ድል ቀንቷቸዋል፡፡
08:00 ላይ በሼር ሜዳ መተሀራ ስኳር ከ ወሊሶ ከተማ ባደረጉት የምድብ ሐ ጨዋታ መተሃራ 1-0 አሸንፏል፡፡ የመተሀራ ሰኳርን ወሳኝ የድል ጎል ያስቆጠረው ፍሬው በቀለ ነው፡፡
ውጤቱን ተከትሎ መተሀራ ስኳር የማለፍ ተስፋውን ሲያለመልም በጥሩ 3ኝነት ለማጠቃለያው ያለፈው ወሊሶ ከተማ ከወዲሁ ከምድቡ ተሰናባች መሆኑን አረጋግጧል፡፡
በ10:00 ሼር ሜዳ ላይ እጅግ ጠንካራ ፉክክር ባስተናገደው ሌላኛው የምድብ ሐ ጨዋታ ካፋ ቡና ከ2-0 መመራት ተነስቶ 4-2 በማሸነፍ ከወዲሁ የሩብ ፍጻሜ ትኬቱን ቆርጧል፡፡
የካፋ ቡናን የድል ጎሎች አንተነህ ከበደ (2) ፣ ምንተስኖት ታረቀኝ እና አሊ አብደላ ሲያስቆጥሩ ቢንያም ጌታቸው እና ብሩክ ክንፈ የአምባሪቾን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የምድብ ሐ ሰንጠረዥ
ክለብ – ተጫ (ልዩነት) ነጥብ
1 ካፋ ቡና 2 (+3) 6
2 መተሃራ ስኳር 2 (+1) 4
3 አምበሪቾ 2 (-2) 1
4 ወሊሶ ከተማ 2 (-2) 0
08:00 ባቱ ሜዳ ላይ በለገጣፎ ከተማ እና ሽረ እንዳስላሴ መካከል ሊካሄድ የነበረው የምድብ መ ጨዋታ ሜዳው ውሃ በመያዙ እስኪስተካከል አንድ ሰአት ዘግይቶ 09:00 ሲጀምር ጨዋታውም ያለግብ ተጠናቋል፡፡
በመጀመርያው ጨዋታ መዘግየት ምክንያት 10:40 የተጀመረው የዳባት ከተማ እና ሶሎዳ አድዋ ጨዋታ በዳባት 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ኃይል የቀላቀለ አጨዋወት በታየበትና ሁለት ተጫዋቾች በቀይ ካርድ ከሜዳ በተወገዱበት ጨዋታ ተመስገን ምትኩ የዳባትን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
የምድብ መ ሰንጠረዥ
ክለብ – ተጫ (ልዩነት) ነጥብ
1 ለገጣፎ ከተማ 2 (+1) 4
2 ሶሎዳ አድዋ 2 (0) 3
3 ዳባት ከተማ 2 (0) 3
4 ሽረ እንዳስላሴ 2 (-1) 1
የመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ቦታ ፣ ሰአት እኛ ቀን ነገ የሚታወቅ ይሆናል፡፡