የኢትዮዽያ ብሔራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ሁለተኛ ዙር ግምገማ እና የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል፡፡
የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ አሊሚራህ መሃመድ ፣የውድድሩ አወዳዳሪ ኮሚቴ አባላት እና የክለብ ተወካዮች በተገኙበት ዛሬ ረፋድ ላይ በባቱ መዘጋጃ ቤት በተካሄደው ግምገማ ላይ የተነሱ የመወያያ ነጥቦች እነዚህን ይመስላሉ፡-
ድክመቶች
* ሜዳዎች ውሃ መያዛቸው ከታወቀ ከጨዋታው አስቀድሞ የሚስተካከሉበት መንገድ ቢፈጠር
* በጥቂት ዳኞች ላይ የሚታየው ጨዋታን የመምራት ብቃት
* በሼር ሜዳ ጨዋታ እንዳይደረግበት ከሼር ስራ አስኪያጅ ተላልፎ የነበረው ውሳኔ
ጠንካራ ጎን
* በየጊዜው የውድድሩን ሂደት በመከታተል የሚደረጉ ግምገማዎች በጥንካሬ ተወስደዋል
*መልካም እንቅስቃሴ ያሳዩ ዳኞች መኖራቸውም በመልካምነቱ ተነስቷል
*የውድድሩ መርሃግብር በታሰበለት ጊዜ መከናወኑ
የተወሰዱ እርምጃዎችና የመፍትሔ ሀሳቦች
* የሜዳ ዝግጅት ዙርያ ከጨዋታው አስቀድሞ በማየት ለማስተካከል ጥረት ይደረጋል
* በዳኝነት ዙርያ የታዩ ግድፈቶችን ለማስተካከል ጥረት እንደሚደረግ ሲገለፅ በዋና ዳኛ መሀመድ ሲራጅ ላይ የእገዳ ውሳኔ ተላልፏል፡፡
በመጨረሻም የመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ላይ ምንም አይነት የመላቀቅ ችግር እንዳይፈጠር ከፍተኛ ትኩረትና ክትትል እንደሚደረግና ሆን ብለው ለመልቀቅ በሚጫወቱ ተጨዋቾች ፣ አሰልጣኞች ፣ የቡድን አመራሮች ላይ በዲሲፒሊን ደንቡ መሰረት ውሳኔ እንደሚሰጥ አሳስበው የስብሰባው ፍፃሜ ሆኗል፡፡
የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች መርሃ ግብር
ቅዳሜ ሐምሌ 23 ቀን 2008
08:00 ወልቂጤ ከተማ ከ አማራ ፖሊስ (ሼር ሜዳ)
08:00 ሞጆ ከተማ ከ ከደሴ ከተማ (ባቱ ሜዳ)
10:00 ዲላ ከተማ ከ አራዳ ክ/ ከተማ (ሼር ሜዳ)
10:00 ቡታጅራ ከተማ ከ ከሚዛን አማን (ባቱ ሜዳ)
እሁድ ሐምሌ 24 ቀን 2008
08:00 መተሃራ ስኳር ከ ካፋ ቡና (ሼር ሜዳ)
08:00 ወሊሶ ከተማ ከ አምበሪቾ (ባቱ ሜዳ)
10:00 ዳባት ከተማ ከ ከሽረ እንዳስላሴ (ሼር ሜዳ)
10:00 ሶሎዳ አደዋ ከ ለገጣፎ ከተማ (ባቱ ሜዳ)