ብሄራዊ ሊግ፡ ከምድብ ሀ እና ለ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀሉ ቡድኖች ታውቀዋል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር 3ኛ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ሲጀምሩ ወደ ሩብ ፍጻሜ ያለፉት ክለቦች ታውቀዋል፡፡

08:00 ላይ ሼር ሜዳ ላይ በተደረገው የምድብ ሀ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ አማራ ፖሊስን 1-0 በማሸነፍ ምድቡን በበላይነት አጠናቋል፡፡ የወልቂጤን ብቸኛ የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈው ጌታነህ ሙሉነህ ነው፡፡

አማራ ፖሊስ ሽንፈት ቢያስተናግድም ደሴ ከተማን በግብ ልዩነት በመብለጥ ወደ ሩብ ፍጻሜው አልፏል፡፡

በዚሁ ምድብ በተመሳሳይ ሰአት በባቱ ሜዳ በተደረገው ሌላ ጨዋታ ደሴ ከተማ ሞጆ ከተማን በተስፋገብርኤል እና እዮብ ካህሳይ ግቦች 2-0 አሸንፏል፡፡

ደሴ ጨዋታውን ቢያሸንፍም በአማራ ፖሊስ በግብ ልዩነት ተበልጦ ከምድቡ ሳያልፍ ቀርቷል፡፡

የምድብ ሀ ሰንጠረዥ

ክለብ – ተጫ (ልዩነት) ነጥብ

1 ወልቂጤ ከተማ    3   (+4)   7

2 አማራ ፖሊስ         3   (+1)   4


3 ደሴ  ከተማ          3   (0)     4

4 ሞጆ ከተማ          3   (-5)    1

በምድብ ለ በሼር ሜዳ 10:00 ላይ ዲላ ከተማ አራዳ ክ/ ከተማን 2-0 በማሸነፍ የሩብ ፍጻሜ ትኬቱን ቆርጧል፡፡ የዲላ የድል ግቦችን ከመረብ ያሳረፉት ዳዊት በቀለ እና የኃላሸት ሰለሞን ናቸው፡፡

ውጤቱን ተከትሎ አራዳ እና ዲላ ተያይዘው ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፍ ችለዋል፡፡

በተመሳሳይ 10:00 ባቱ ሜዳ ላይ ቡታጅራ ከተማ ሚዛን አማንን በአብደላ መሃመድ ጎል 1-0 ቢያሸንፍም ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ በቂ አልሆነለትም፡፡

የምድብ ለ ሰንጠረዥ

ክለብ – ተጫ (ልዩነት) ነጥብ

1 አራዳ                  3   (+3) 6

2 ዲላ ከተማ          3   (+2) 6


3 ቡታጅራ ከተማ   3   (-2)  6

4 ሚዛን አማን        3   (-3)  0

የነገ ጨዋታዎች

ምድብ ሐ

እሁድ ሐምሌ 24 ቀን 2008

08:00 መተሃራ ስኳር ከ ካፋ ቡና (ሼር ሜዳ)

08:00 ወሊሶ ከተማ ከ አምበሪቾ (ባቱ ሜዳ)

ምድብ መ

10:00 ዳባት ከተማ ከ ከሽረ እንዳስላሴ (ሼር ሜዳ)

10:00 ሶሎዳ አደዋ ከ ለገጣፎ ከተማ (ባቱ ሜዳ)

1 Comment

Leave a Reply