የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር የምድብ ሐ እና መ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደዋል፡፡ ወደ ሩብ ፍጻሜ የተሸጋገሩ ክለቦችም ታውቀዋል፡፡
08:00 ላይ በሼር ሜዳ መተሃራ ስኳር ካፋ ቡናን 2-1 በማሸነፍ ምድቡን በበላይነት አጠናቋል፡፡ የመተሃራ ስኳርን የድል ግቦች ዮርዳኖስ ዮሃንስ እና አረጋከኝ ለማ ሲያስቆጥር አሊ አብዲ የካፋ ቡናን ግብ አስቆጥሯል፡፡
በተመሳሳይ 08:00 ባቱ ሜዳ ላይ አምበሪቾ ወሊሶ ከተማን 5-2 ቢያሸንፍም ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ በቂ አልሆነለትም፡፡
ቢንያም ጌታቸው 3 ግቦች አስቆጥሮ ሐት-ትሪክ ሲሰራ ደበላ ሮባ እና ወንደሰን ምህረቴ ቀሪዎቹን የሀምበሪቾ ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ሙሴ ባንቲ እና ዳንኤል በሃይሉ የወሊሶን ግቦች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
የምድብ ሐ ሰንጠረዥ
ክለብ – ተጫ (ልዩነት) ነጥብ
1 መተሃራ ስኳር 3 (+2) 7
2 ካፋ ቡና 3 (+2) 6
– – – – – – – –
3 አምበሪቾ 3 (+1) 4
4 ወሊሶ ከተማ 3 (-5) 0
በምድብ መ 10:00 ላይ በሼር ሜዳ ሽረ እንዳስላሴ ዳባት ከተማን 3-1 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል፡፡
ከሊል ሃሰን ፣ ያሬድ ወ/ገብሬል እና አቤል መብራቱ የሽረን ግብ ሲያስቆጥሩ ፊሊሞን ተኩ የዳባትን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል፡፡
በተመሳሳይ ሰአት ባቱ ሜዳ ላይ ለገጣፎ ከተማ ሶሎዳ አድዋን 3-2 በማሸነፍ ምድቡን በበላይነት አጠናቋል፡፡ አስናቀ ተሽፊዬ እና ሱሉቶ አለሙ (2) የለገጣፎን ግብ ሲያስቆጥሩ ጂብሩል ጁነይዲ እና በፍቃዱ አለማየሁ የሶሎዳን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የምድብ መ የደረጃ ሰንጠረዥ
ክለብ – ተጫ (ልዩነት) ነጥብ
ለገጣፎ ከተማ 3 (+2) 7
ሽረ እንዳስላሴ 3 (+1) 4
– – – – – – – –
ሶሎዳ አድዋ 3 (-1) 3
ዳባት ከተማ 3 (-2) 3
* ውድ አንባቢዎቻችን በባቱ ከተማ የስልክ ኔትዎርክ በመቋረጡ ከሪፖርተራችን በፍጥነት መረጃዎችን መቀበል አልቻልንም፡፡ መረጃዎችን በዚህ ምክንያት ለማዘግየት መገደዳችንን ለማሳወቅ እንወዳለን