ጅማ አባ ቡና ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደጉን አረጋገጠ

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ዛሬ ከወራቤ ከተማ ጋር ተስተካካይ ጨዋታውን ያደረገው ጅማ አባ ቡና ካለ ግብ አቻ ተለያይቶ ወደ ፕሪሚየር ሊግ መግባቱን ከወዲሁ አረጋግጧል፡፡

ከ25 ጨዋታዎች 61 ነጥቦችን የሰበሰበው ጅማ አባ ቡና 3ኛ ደረጃ ሊላይ ከሚገኘውና 26 ጨዋታ ካደረገው ወራቤ ከተማ በ13 ነጥቦች ርቆ በመቀመጡ ለከርሞ ወደ ሃገሪቱ ትልቅ ሊግ መሸጋገሩን አረጋግጧል፡፡

በ1947 በጅማ እርሻ ኮሌጅ አማካኝነት የተመሰረተው ጅማ አባ ቡና ከአመታት በፊት ከኢትዮጵያ እግርኳስ ካርታ ጠፍቶ በ2006 እንደገና በመመስረት በ3 አመታት ውስጥ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ አድጓል፡፡

PicsArt_1470061935120

ጅማ አባ ቡና ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያደገ በታሪክ የመጀመርያው የጅማ ክለብ ሲሆን በፕሪሚየር ሊጉ የተሳተፈ 43ኛው ክለብ ለመሆን በቅቷል፡፡ በ1990ዎቹ መጀመርያ ጥቂት የሙገር ሲሚንቶ ጨዋታዎችን ከማስተናገድ ውጪ በፕሪሚየር ሊጉ ስም የሌላት ጅማ ከተማም በቀጣዩ አመት በሊጉ የሚወክላት ክለብ አግኝታለች፡፡

PicsArt_1470061888681

በጅማ አባቡና ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደግ ዙርያ ከክለቡ አሰልጣኝ እና ተጫዋቾች ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ከቆይታ በኋላ ይዘን እንመለሳለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *