በዛሬው እለት ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን ያረጋገጠው ጅማ አባ ቡና ከወዲሁ የፕሪሚየር ሊግ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን መሰብሰብ ጀምሯል፡፡
ጅማ አባ ቡና ከ5 ተጫዋቾች ጋር በቃል ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሱ የታወቀ ሲሆን በመጪዎቹ ቀናት በይፋ ከክለቡ ጋር ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የመከላከያ ውሉን የጨረሰው መሃመድ ናስር ወደ ትውልድ ከተማው የሚመልሰውን ዝውውር ሲያደርግ ከመከላከያ ጋር በውል ማራዘም ላይ ከስምምነት መድረስ ያልቻለው የብሄራዊ ቡድኑ ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሰውም አጥቂውን ተከትሎ ወደ ጅማ አምርቷል፡፡
በውድድር ዘመኑ ድንቅ አቋም ያሳየው የወላይታ ድቻው የአጥቂ አማካይ በድሉ መርዕድ ሌላው ለጅማ አባ ቡና ለመፈረም የተስማማ ተጫዋች ሲሆን የክለብ አጋሩ ኃይለየሱስ ብርሃኑም ጅማ ደጃፍ ደርሷል፡፡ ኃይለየሱስ በተከላካይ እና አማካይነት መጫወት የሚችል ተጫዋች ነው፡፡
አስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ በሚቆይ ውል ኤሌክትሪክን ያገለገለው ፍጹም ገብረማርያም ሌላው ለጅማ አባ ቡና ለመፈረም የተስማማ ተጫዋች እንደሆነ ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ቢያመለክትም በዩናይትድ ስቴትስ የእረፍት ጊዜውን እያሳለፈ የሚገኘው የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ኮከብ ከክለቡ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳላደረገ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡ በቀጣዩ ሳምንት ወደ ሀገር ቤት ሲመለስ ቀጣይ ማረፊያውን እንደሚወስንን ጨምሮ ተናግሯል፡፡
ለአባ ቡና ለመፈረም ከስምምነት ከደረሱት ተጫዋቾች መካከል መስኡድ መሃመድ አንዱ ነው፡፡ መስኡድ ከቡና ጋር ያለው ኮንትራት እስካሁን ያልታደሰ ሲሆን በክለቡ ያለውን ቆይታ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡
ጅማ አባ ቡና በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳታፊ መሆን የቻለ ሲሆን በቀጣዩ የውድድር ዘመን ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ ስራዎች እየሰራ እንደሆነ ከክለቡ አካባቢ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሐምሌ 26 ቀን 2008 ዓ.ም
አመለ ሸጋው የየኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አምበል መስዑድ መሐመድ ውሉን አራዘመ፡፡
አመለ ሸጋው የየኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አምበል መስዑድ መሐመድ ስሙ ከሌላ ክለብ ጋር ሲነሳ ቢቆይም በክለባችን ሬዲዮ ፕሮግራም ቀርቦ በገባው ቃል መሠረት ዛሬም ለየኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ታማኝነቱን በማሳየት ለ2ዓመት የሚያቆየውን ውል ተፈራረመ፡፡
Mesud has put his signature to Ethiopian Coffee. Bravoooooooooooooooooooooooooo
አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረምና ለፕሪሜር ሊግ ዝግጅቸት በቂ ዕረፍት ለማድረግ ግዜው አጭር ስለሚሆንብን ፌደሬሽኑ ሊያስብበት ይገባል፡፡ otherwise it’s unfair.
Well done Jimma Coffee. The love for sport in general and football in particular is unparalleled. About time the PL went to Jimma and the likes of St G going to there is going to take football to the next level for the passionate fans in Jimma.
Hope to be in town one of these days when the big name clubs are playing. At the mo, Im 9000kms away!
Bertu Yejimma Kuratoch Be Premier Ligum asgerami wutet Entebikalen.
Jimma Ababunaa Pride of Jimma Town!!
jimma abba buna tarikin bworki ystafe jegna kilab nw.jimma abba buna my hero