ፌቮር ኢማኑኤል ከሃገሩ አልተመለሰም

በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር ከኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ዳሸን ቢራን የተቀላለቀለው ካሜሩናዊው ግብ ጠባቂ ፌቮር ኢማኑኤል የሊጉን ለረጅም ጊዜያት መቋረጥን ተከትሎ በክለቡ የተሰጠውን እረፍት ተጠቅሞ ሃረጉ ቢሄድም እስካሁን እንዳልተመለሰ ሃት-ትሪክ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

ዳሸን ቢራ ለቀድሞው የመብራት ኃይል ግብ ጠባቂ ዝውውር 350 ሺህ ብር ወጪ ያደረገ ሲሆን ላለፉት 6 ወራት በወር 20 ሺህ ብር ሲከፍለው ቆይቷል፡፡ ፌቮ በእሁዱ የዳሸን ቢራ እና መብራት ኃይል ጨዋታ ላይ ያልነበረ ሲሆን እስካሁን ያልተመለሰበት ምክንያት የመኖርያ እና የስራ ፈቃድ ባለማግኘቱ ነው፡፡ ክለቡ ዳሸንም የተጫዋቹን ዶክመንት ሳያገናዝብ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

ፌቮ እስከወዲያኛው የማይመለስ ከሆነ ዘንድሮ ብቻ የፊርማ ክፍያ ተቀብሎ የኮበለለ 3ኛው ተጫዋች ይሆናል፡፡ ለአህሊ ሼንዲ ፈርሞ ሐዋሳ ከነማ በውሰት ሲጫወት የነበረው ታፈሰ ሰለሞን ለ1 አመት 400 ሺህ ብር ተቀብሎ ወደ ሱዳን ያመራ ሲሆን ካሜሩናዊው አማካይ ታሚ ኩፔም ከመብራት ኃይል የ2 አመት 650ሺህ ብር ተቀብሎ ወደ ሃገሩ ኮብልሏል፡፡

ይህ የክለቦቻችን ፕሮፌሽናል መንገድ ያልተከተለ የዝውውር እንቅስቃሴ ያመጣው መዘዝ ክለቦቻችንን ለትልቅ ኪሳራ እየዳረጋቸው ነው፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ