ሀዋሳ ከተማ ፍሬው ሰለሞንን አስፈረመ

በክረምቱ ዋነኛ የዝወውር አጀንዳ ከነበሩት ተጫዋቾች አንዱ የነበረው ፍሬው ሰለሞን ለሀዋሳ ከተማ መፈረሙ ተረጋግጧል፡፡

ፍሬው የመከላከያ ኮንትራቱን እንደማያድስ ከተረጋገጠ በኋላ ለቅዱስጊዮርጊስ ለመፈረም በእጅጉ ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም በይፋ የሚፈርምበት ቀን በመዘግየቱ ሳይፈርም ቀርቷል፡፡ በመጨረሻም ሀዋሳ ከተማ ከአማካዩ ጋር የተሳካ ድርድር አድርጎ ወደ ክለቡ ጠቅልሎታል፡፡

ፍሬው ለሀዋሳ የፈረመው ለ2 አመት እንደሆነ የታወቀ ሲሆን የክለቡን የአማካይ ክፍል አማራጭ ያሰፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

PicsArt_1467225480464

በተመሳሳይ የክለቡ ዜና በውድድር ዘመኑ መባቻ ጫማውን በይፋ የሰቀለው ሙሉጌታ ምህረት የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ረዳት ሆኖ ለመሾም ተቃርቧል፡፡

አሰልጣኝ ውበቱ የክለቡን ታላቅ ተጫዋች ረዳታቸው እንዲሆን የመረጡት ሲሆን የሚጠበቀው የክለቡ ኃላፊዎች የአሰልጣኙን ጥያቄ በይፋ እስኪቀበሉ ብቻ ነው፡፡

2 Comments

  1. I think in next session Hawassa will back to it’s Greatness & we will be champion ones again.

Leave a Reply