የ2008 የውድድር ዘመን የኢትዮዽያ ብሄራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ደርሷል፡፡
ከሐምሌ 15 ጀምሮ በባቱ ከተማ የተካሄደው ውድድር በአራት ምድብ ተከፍሎ በ16 ክለቦች መካከል ቁጥሩ በርካታ ተመልካች በተገኘበት በድምቀት ሲካሄድ ቆይቶ የሩብ ፍጻሜ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
በውድድሩ 24 ጨዋታዎች የተካሄዱ ሲሆን 64 ጎሎች ከመረብ አርፈዋል፡፡ በአማካይ 2.67 ግቦች በየጨዋታው ያርፋሉ ማለት ነው፡፡ ከግቦች ጋር የሚስተካከል 61 የቢጫ ካርድ እና 2 ቀይ ካርዶችም ተመዝግበዋል፡፡
በውድድሩ 6 ክለቦች ወደ ከፍተኛ ሊግ የሚሻገሩ ሲሆን ነገ እና ከነገ በስቲያ የሚደረጉትን የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች የሚያሸንፉ ክለቦች በቀጥታ ወደ ከፍተኛ ሊግ ማለፋቸውን ያረጋጋግጣሉ፡፡
የሩብ ፍጻሜ ተሸናፊዎች ወደከፍተኛ ሊግ ለመግባት በድጋሚ እጣ ወጥቶላቸው እርስ በእርስ የሚጫወቱ ሲሆን የሚያሸንፉ ሁለት ክለቦች 5ኛ እና 6ኛ ሆነው ከፍተኛ ሊጉን ይቀላቀላሉ፡፡
የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች
ረቡዕ ሐምሌ 27 ቀን 2008
08:00 ወልቂጤ ከተማ ከ ዲላ ከተማ
10:00 አማራ ፖሊስ ከ አራዳ ክ/ከተማ
ሐሙስ ሐምሌ 28 ቀን 2008
08:00 መተሀራ ስኳር ከ ሽሬ አንደስላሴ
10:00 ከፋ ቡና ከ ለገጣፎ ከተማ
ከዚህ በኋላ የሚደረጉት ሁሉም ጨዋታዎች በባቱ ሜዳ ሲከናወኑ ጨዋታዎች በዘጠና ደቂቃ በአቻ ውጤት የሚጠናቀቁ ከሆነ በቀጥታ ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ያመራሉ፡፡