ኤልያስ ማሞ የከፍተኛ ደሞዝ ደረጃውን ይመራል

የኢትዮጵያ እግርኳስ የዝውውር መስኮት ከተከፈተ ዛሬ 28ኛ ቀኑን ይዟል፡፡ የኢትዮጵያ  እግርኳስ ፌዴሬሽንም በዚህ ወር በይፋ በፌዴሬሽኑ በመገኘት የፈረሙ ተጫዋቾችን ዝርዝር በከፊል ለሚድያ ይፋ አድርጓል፡፡

በኢትዮጵያ እግርኳስ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ተጫዋቾች የውል ጊዜያቸው እስኪጠናቀቅ ተጠብቆ አዲስ ውል ይፈራረማሉ፡፡ ከባለፈው አመት ጀምሮ በወጣው ህግ መሰረትም ተጫዋቾች የተስማሙበትን ገንዘብ በአንድ ጊዜ ሳይሆን በየወሩ ተከፋፍሎ ያገኛሉ፡፡

ፌዴሬሽኑ ይፋ ባደረገው መሰረት የኢትዮጵያ ቡና ውሉን ያደሰው ኤልያስ ማሞ በወርሃዊ 95,135 ብር ከፍተኛው ደሞዝተኛ ሆኗል፡፡

በዝርዝሩ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ለመከላከያ አዲስ ውል የፈረመው ቴዎድሮስ በቀለ እና ሲዳማ ቡናን ለቆ ወደ መከላከያ የተመለሰው አወል አብደላ ወርሃዊ 88,724 ብር ያገኛሉ፡፡

የዘንድሮው የደሞዝ ጣርያ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር የ28ሺህ ብር ልዩነት ያስመዘገበ ሲሆን የዝውውር መስኮቱ እስከ ጥቅምት መጀመርያ የሚቆይ በመሆኑ የደሞዝ ጣርያው ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

ፌዴሬሽኑ ይፋ ያደረጋቸው ውሎች በከፊል የሚከተሉት ናቸው፡-

PicsArt_1470322005613

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *