አፍሪካ ፡ ኤኳቶሪያል ጊኒ ከሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆናለች

በአህጉሪቱ የሴቶች እግርኳስ ከናይጄሪያ በመቀጠል የአፍሪካ ዋንጫው ማንሳት የቻለችው ኤኳቶሪያል ጊኒ ካሜሮን ከምታስተናግደው የቶታል የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ውጪ እንድትሆን ካፍ ትላንት ባስተላለፈው የቅጣት ውሳኔ ገልጿል፡፡

ኤኳቶሪያል ጊኒ በ2018 እና 2020 ከሚደረገው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫም ውጪ እንድትሆን ቅጣት ተላልፎባታል፡፡

በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኤኳቶሪያል ጊኒን የገጠመችው ማሊ ካሚላ ኖብሬ በተባለችው ተጫዋች ላይ ባቀረበችው የተገቢነት ጥያቄ ምክንያት ካፍ ቅጣቱን ሊያስተላለፍ ችሏል፡፡ ካሚላ ኖብሬ በ2014 የናሚቢያው የአፍሪካ ዋንጫ የፖስፖርት የልደት ቀኗ 7/10/1994 የተመገበ ሲሆን ከማሊ ጋር በተደረገው ጨዋታ ላይ የቀረበው የፖስፖርት የልደት ቀን 10/06/1988 እና ስም ልዩነት መኖሩ ካፍ ኤኳቶሪያል ጊኒን በማጭበርበር ቅጣት አስተላልፎባታል፡፡ የኤኳቶሪያል ጊኒ እግርኳስ ፌድሬሽን የተጫዋቿን ሪከርድ ለማስተካከል ከካፍ ጋር ድርድር ያላደረገ ሲሆን ማሊን በድምር ውጤት 3-2 የረታው ብሄራዊ ቡድን ውስጥ የተካተተችው ካሚላ ለጨዋታው ተገቢ አልነበረችም ተብሏል፡፡

ካፍ በውሳኔው ማሊን ወደ አፍሪካው ዋንጫው እንድታልፍ አድርጓል፡፡ ኤኳቶሪያል ጊኒ በወንዶችም በሴቶችም እግርኳስ ከሃገሪቱ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸውን ተጫዋቾች በብሄራዊ ቡድኗ በማካተቷ በተደጋጋሚ ስትተች ቆይታለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *