በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ወደ ከፍተኛ ሊግ የሚገቡ የመጨረሻ 2 ክለቦችን ለመለየት ዛሬ ረፋድ የእጣ ማውጣት ስነስርአት ተካሂዷል፡፡
በወጣው እጣ መሰረት መተሃራ ስኳር ከ ካፋ ቡና ሲጫወት አማራ ፖሊስ ከ ዲላ ከተማ ሌሎቹ ተጋጣሚዎች ናቸው፡፡
በሩብ ፍጻሜው ተሸንፈው ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍ ሳይችሉ የቀሩት አራቱ ክለቦች በእጣው መሰረት ነገ በሚያደርጉት ጨዋታ 5ኛ እና 6ኛ ሆነው ወደ ከፍተኛ ሊግ ለማለፍ የመጨረሻ እድላቸውን ይሞክራሉ፡፡
ወልቂጤ ከተማ ፣ አራዳ ክ/ከተማ ፣ ለገጣፎ ከተማ እና ሽረ እንዳስላሴ ወደ ከፍተኛ ሊጉ ማደጋቸውን ከወዲሁ ያረጋገጡ ክለቦች ናቸው፡፡
ወደ ከፍተኛ ሊግ ለመግባት የመለያ ጨዋታ
ቅዳሜ ሐምሌ 30 ቀን 2008
08:00 መተሃራ ስኳር ከ ካፋ ቡና (ባቱ ሜዳ)
10:00 አማራ ፖሊስ ከ ዲላ ከተማ (ባቱ ሜዳ)
የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች
እሁድ ነሀሴ 1 ቀን 2008
08:00 ለገጣፎ ከተማ ከ ሽረ እንዳስለሴ (ባቱ ሜዳ)
10:00 አራዳ ክ/ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ (ባቱ ሜዳ)